BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ 'የሸኔ ታጣቂዎች' ከ40 በላይ ሰዎች መግደላቸውን ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት ተናገሩ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሸኔ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሕጻናትና ነፍሰ ጡር እናቶችን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ። ታጣቂዎቹ ጥቃቱን በምዕራብ ኢትዮጵያ በምትገኘው ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ውስጥ የተፈጸመው ቅዳሜ ኅዳር 13/2018 ዓ.ም. ነው።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ አገልግሎት: ከ60 ዓመታት በኋላ ዳግም ይመለስ ይሆን?
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚያልፉ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት በተለያዩ መስኮች ላይ የሚሰማሩበት አሠራር ሲታሰብ ቆይቷል። ከሳምንት በፊት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ አገልግሎት በመጪው ዓመት ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ከተናገሩ በኋላ መነጋገሪያ ሆኗል። ይህ አገልግሎት ከ50 ዓመታት በፊት የነበረ ሲሆን ተቋርጦ ቆይቶ አሁን ዳግም ለማስጀመር ታስቧል። በዚህ ዕቅድ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦች እየተሰነዘሩ ሲሆን፣ ይህ ዘገባ ታሪካዊ ዳራውን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ይዳስሳል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች

ቪዲዮ,አምስት ዓመት ያስቆጠረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ይቀሰቀስ ይሆን?
በትግራይ የተካሄደው ጦርነት አምስት ዓመት ሆነው። ጦርነቱ ከፍተኛ ውድመት ከማስከተሉም በላይ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ በርካታ ክስተቶችን ፈጥሯል። ጦርነቱን ያስቆመው የፕሪቶሪያው ግጭት የማቆም ስምምነት ባለፉት ሦስት ዓመታት አንጻራዊ ሰላም አምጥቷል። የሰላም ስምምነቱ ሦስተኛ ዓመት እየተዘከረ ባለበት በዚህ ወቅት የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት እየተወነጃጀሉ ነው። ይህ መካሰስ ወደ ጦርነት ያመራ ይሆን?

ቪዲዮ,የጋዛ ጦርነት በመካከለኛው ምሥራቅ የፈጠረው የኃይል ሚዛን ለውጥ
ለሁለት ዓመት የተካሄደው የጋዛ ጦርነት 70 ሺህ የሚጠጉ ፍልስጤማውያንን ሕይወት ቀጥፏል። በኢራን እና በእስራኤል መካከል የቀጥታ ጦርነት ምክንያት ሆኗል። ከመካከለኛው ምሥራቅ እየራቀች የነበረችው አሜሪካ በዚሁ ጦርነት ሳቢያ ተጎትታ ወደ ቀጠናው ተመልሳለች። በአንጻሩ ሩሲያ በቀጠናው የነበራትን ይዞታ ለማጣት ተገዳለች። አጋሮቻቸውን የጋዛ ጦርነት ያዳከመባቸው የሶሪያው ባሻር አል አሳድ ከ13 ዓመት የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ከስልጣን ተወግደዋል። ይህ ቪዲዮ የሁለት ዓመቱ የጋዛ ጦርነት ከመካከለኛው ምሥራቅ ባለፈ በመላው ዓለም የፈጠረውን ለውጥ ይዳስሳል።

ቪዲዮ,ኢሉሚናቲዎች መነሻቸው ከየት ነው? እውን ዓለምንስ በምሥጢር 'ይቆጣጠራሉ'?
"ኢሉሚናቲዎች በምሥጢር ዓለምን ተቆጣጥረው አዲስ ሥርዓት ሊዘረጉ ነው" የሚለው መላ ምት ለዓመታት ሲሰማ ቆይቷል። የዚህ ሃሳብ መነሻ በአውሮፓውያኑ 1960ዎቹ የነበረ ልብ ወለዳዊ ክስተት ነው። ባቫሪያን የሚባል ምሥጢራዊ ስብስብ ነበር።ይህም እአአ በ1776 ነበር የተጀመረው። ወግ አጥባቂ እና ክርስቲያን ተቺዎች ግን አልተቀበሏቸውም። ለተወሰነ ጊዜ ጠፍተው በ1960ዎቹ ዳግመኛ አንሰራሩ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ስለባሕር በር፣ ስለድርድር እና ስለምርጫ ምን አሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዓመቱ የመጀመሪያውን ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህም በምጣኔ ሀብት፣ በምርጫ፣ በባሕር በር እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለሰዓታት የዘለቀ ሰፊ ምላሽ ሰጥተዋል። በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ መንግሥት ዋነኛ አጀንዳ የሆነው የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ጉዳይን በስፋት አብራርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበትን ውሳኔ ማን እንዳሳለፈ የሚታወቅ ነገር እንደሌለ እና መንግሥታቸው “የቀይ ባህር ጉዳይ ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው” ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል።

ቪዲዮ,ኃያላኑ ሀገራት የተፋጠጡበት አርክቲክ ለምን ተፈላጊ ሆነ?
አሜሪካ፣ ሩሲያ እና ቻይና በአርክቲክ ዙሪያ እያንዣበቡ ነው። ዓመቱን ሙሉ በረዶ የማያጣው የሰሜኑ ጫፍ በኃያላን ሀገራት መካከል ፍጥጫ እንዲኖር ምክንያት ሆኗል። የሩሲያ እና የአሜሪካ ተዋጊ ጄቶች በቅርብ ርቀት ሲበሩ ታይተዋል። በርካታ ሀገራት የጦር ልምምድ እና የሚሳኤል መኩራ የሚያደርጉት በአርክቲክ ነው። ቻይናም ሩሲያን ተጠግታ በአርክቲክ አካባቢ እንቅስቃሴ ጀምራለች። ለመሆኑ አርክቲክ ተፈላጊ የሆነው ለምንድነው? እነሆ 5 ምክንያቶች

በዱባይ የሚካሄደውን የሴቶች ብዝበዛ እና የወሲብ ንግድ የሚያንቀሳቅሰው ማነው?
አንድ ሰሞን ከወደ ዱባይ የሚመጡ ዜናዎች አስደናጋጭ እና አስፀያፊ ነበሩ። በማኅበራዊ ሚድያ ‘ዱባይ ፖታ ፓርቲ’ የተሰኘ ስም የተሰጠው ይህ ክስተት ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። የዱባይ ሀብታሞች ሴቶች ላይ ሲፀዳዱ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ወጥተዋል። ይህ ቪድዮ ከወጣባቸው ሴቶች መካከል ሁለቱ ከፎቅ ራሳቸውን ወርውረው ሞተዋል። ለመሆኑ ይህን ‘የዱባይ ፖታ ፓርቲ’ የሚያንቀሳቅሰው ማነው? ሴቶችን አማልሎ የሚወስደውስ እንዴት ነው? ይህ የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ምላሽ ይዟል
አነጋጋሪ ጉዳይ

"ቢገድሉኝ ይሻል ነበር"፡ የሴቶችን ሕይወት እያበላሸ ያለው የተዘነጋው የአማራ ክልል ጦርነት
ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ግጭቱ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ሰቆቃ ትኩረትን አላገኘም። ቢቢሲ ለወራት ባካሄደው ክትትል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የመደፈር እና የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መረጃ አግኝቷል።

ቦይንግ አውሮፕላኖችን በመግዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስራ አንድ ቦይግን 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት መዋዋሉን አስታውቋል። አየር መንገዱ እና ቦይንግ ከዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዱባይ ከተማ ሰኞ ዕለት በተካሄደው ዓለም አቀፍ የአውሮፕላኖች ኤግዚቢሽን ላይ ነው። ከቦይንግ አውሮፕላኖችን በብዛት በመግዛት የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሚፎካከሩ የአፍሪካ አየር መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ከተገደለ ከአስርታት በኋላ መነጋጋሪያ ሆኖ የቀጠለው ቶማስ ሳንካራ ማን ነው?
ቶማስ ሳንካራን ምን ገደለው? ይህ ጥያቄ ከ34 ዓመታት በኋላም ትክክለኛ ፍርድ አግኝቶ ምላሽ አልተሰጠበትም። ደጋፊዎቹ ሕዝቡን ይወዳል፤ አገሩን ይወዳል፤ አፍሪካን ይወዳል፤ ሲሉ ስሙን እያነሱ ያዜሙለታል። ይህ የእሱ ትክክለኛው መገለጫው አይደለም የሚሉ ተቺዎች ደግሞ ለተቃዋሚዎቹ ዕድል የማይሰጥ ሲሉ ይወቅሱታል። ሳንካራ ከተገደለ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ቢሆንም በቡርኪናፋሶ ዜጎች ዘንድ አልተዘነጋም።

የኤርትራን "የግዛት አንድነት ጥሰቶች" በተመለከተ መንግሥት የያዘው "የመታቀብ" አቋም "ሁሌም እንደማይቀጥል" ዶ/ር ጌዲዮን አሳሰቡ
ኤርትራ በኢትዮጵያ "ሉዐላዊነት እና የግዛት አንድነት" ላይ የምትፈጽማቸው "ጥሰቶችን" በተመለከተ የፌደራል መንግሥት የያዘው እርምጃ ከመውሰድ "የመታቀብ" አካሄድ "ሁሌም የሚቀጥል እና ገደብ የለሽ ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት" የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ።ዶ/ር ጌዲዮን፤ ኢትዮጵያ "ከኤርትራ መገንጠል በፊት እና በኋላ" በአሰብ ወደብ ላይ "ባፈሰሰችው ከፍተኛ ሀብት ምክንያት"፤ አሰብ በፌደራል መንግሥት "በዋነኛነት ቅድሚያ የሚሰጠው" ጉዳይ እንደሆነ መግለጻቸውም ተዘግቧል።

"የባሕር በር ካላገኘን ጦርነት ይኖራል" ያሉት የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት እና የኬንያ ስጋት
ኡጋንዳን አራት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ የመሩት ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አገራቸውን ወደ ሕንድ ውቅያኖስ የሚያደርስ የባሕር በር እና የባሕር ኃይል እንዲኖራቸው እንደሚፈልጉ በይፋ ተናግረዋል። ይህ የፕሬዝዳንቱ ፍላጎት ደግሞ ያነጣጠረው በጎረቤት ኬንያ ላይ መሆኑ በኬንያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። ሙሴቬኒ አገራቸው የባሕር መተላለፊያ ካላገኘች በአካባቢው ወደፊት ለሚከሰት ጦርነት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ለሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ማርበርግ ቫይረስ መሆኑ ታወቀ፤ ክትባት ወይም መድኃኒት አለው?
በደቡብ ኢትዮጵያ በጂንካ ከተማ ተከስቶ ለስድስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው በሽታ ማርበርግ ቫይረስ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። ከኢትዮጵያ በስተደቡብ በሚገኙ አገራት ውስጥ ተከስቶ የነበረው ይህ በሽታ ከሳምንት በፊት ነው በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ተከስቶ ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎችን የገደለው።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ

መጥፎ ጓደኛ ላለመሆን የሚረዱ አምስት ቀላል መንገዶች
እንዲኖረን የምንፈልገው ዓይነት ጓደኛ ለመሆን ማሻሻል ያለብን ባህሪዎች የትኞቹ ናቸው? እንዴትስ መጎ ጓደኛ መሆን ይቻላል? እነዚህ የብዙዎች ጥያቄ ናቸው።አንደኛው ጥሩ ጓደኛ መሆን የሚቻልበት መንገድ ተቃራኒ ማንነትን ማስወገድ ነው። ቋሚ መሆንን ጨምሮ በጎ ወዳጅ መሆን የሚቻልባቸውን መንገዶች እንመልከት።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!

በብርሌ ፍቅር የወደቁት ፈረንጅ 'ብርሌ ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ አለ' ይላሉ
ሰሞኑን አረቄ ብሔራዊ አጀንዳ ሆና የማኅበራዊ ሚዲያ አናት ላይ ወጥታ ነበር። ጠጅ ቢሆን አናት ላይ አይወጣም፤ ወደ ጉልበት ነው የሚወርደው። ጠጅ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳይ ሆኖ የሥነ መንግሥቱ አናት ላይ ወጥቶ፣ 'ብሔራዊ አጀንዳ' የነበረው በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ዘመን ነው። ድሮ ጠጅ በብርሌ ይቀርብ ነበር። ከዚያ በብርሌ ይጠጣ ጀመር። ጠጅ ግን እንደ አረቄ ማንም ‘ተራ ዜጋ’ ብድግ አድርጎ አያንደቀድቀውም።ብርሌ ውስጥ የመደብ ታሪክ አለ። የዘመን ታሪክ አለ። የጭሰኛና የመሳፍንት ታሪክ አለ። ያልተሳከረ።

ግመሎችን እና ወርቅ በመሸጥ ሃብት ያካበቱት፣ አሁን ደግሞ ከፊል ሱዳንን የሚቆጣጠሩት ሐምዳን ዳጎሎ
ሞሐመድ ሐምዳን ዳጎሎ ወይም "ሄሜቲ" ከሚመሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር በመሆን በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኑ እና አሁን የአገሪቱን ግማሽ የሚቆጣጠሩ ግለሰብ ናቸው። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የአገሪቱ ጦር እና አጋሮቹ በምዕራብ ዳርፉር የምትገኘውን የጦሩ መቀመጫ የኤል ፋሸር ከተማን በእጁ ሲያስገባ አስደናቂ ድል አግኝቷል።

እየተስፋፋ የመጣውን የካንሰር በሽታን በአመጋገብ መከላከል እና መፈወስ ይቻላል?
የአመጋገብ ለውጥ በማድረግ እና ከመደበኛው ሕክምና ውጪ ያሉ አማራጭ ሕክምናዎችን በመጠቀም ከካንሰር ማገገማቸውን የሚናገሩ አሉ። ለዚህም የተለያዩ ዓይነት ምግቦች፣ ቅመማ ቅመሞች እና እንቅስቃሴዎች በዓለም ዙሪያ ካንሰርን ይከላከላኑ እንዲሁም ይፈውሳሉ በሚል ጥቅም ላይ በስፋት እየዋሉ ነው። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይም እየተጋሩ መነጋገሪያ ከሆኑ ሰንበትበር ብለዋል። ባለሙያዎች ምን ይላሉ? እውን ለሕመሙ መፍትሄ ይሰጣሉ?
የእስራኤል እና የኢራን ግጭት

በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል የሆነችው የአይሁዶች አገር እስራኤል እንዴት ተመሠረተች?
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል እና ብቸኛዋ የአይሁዶች አገር የሆነችው እስራኤል በዙሪያዋ ካሉ አገራት ሁሉ በዕድሜ ትንሿ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ በአውሮፓውያኑ 1948 የእስራኤል እንደ አገር መመሥረት በአካባቢው አሁን ድረስ እየተካሄደ ያለ ለውጥን አስከትሏል። ለመሆኑ በየዕለቱ የዓለም መገናኛ ብዙኃን ስሟን ሳያነሱ የማያልፏት ይህች አገር እንዴት ተመሠረተች?

እስራኤል 15 የጦር አውሮፕላኖችን አሰማርታ ኳታር ውስጥ የፈጸመችው ጥቃት
በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ እስራኤል ጥቃት የፈጸመችው በርካታ የሐማስ ፖለቲካ ቢሮ ባለሥልጣናት በሚኖሩበት የመኖሪያ አካባቢ ላይ ነው። በዚህ ጥቃት አስከ ስምንት የሚደርሱ ፍንዳታዎችን እና ከፍተኛ ጭስ በዶሃ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ማየታቸውን ዓይን እማኞች ተናግረዋል። ከጥቃቱ ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እስራኤል ለተፈጸመው ጥቃት በይፋ ኃላፊነቱን ወስዳለች።

የእስራኤል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ተጠይቆ የነበረው ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን
የጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ቤን ጉርዮን መንግሥት በዓለም ታዋቂ የሆነው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ለእስራኤል ፕሬዝዳንትነት እንዲሆን ካጩት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤል አምባሳደር አባ ኢባን አንስታይንን እንዲያነጋግሩ ተደረገ።

ሐማስ በጋዛ ከሚደረገው ጦርነት ተርፎ ኅልውናው ሊቀጥል ይችላል?
ሁለት ዓመት ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት በጋዛ ሰርጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ የግዛቲቱ አብዛኛው ክፍል ፈራርሷል። እስራኤል ዘመቻዋን ስትጀምር ያስቀመጠቻቸው ታጋቾችን የማስለቀቅ እና ሐማስን የመደምሰስ ዕቅዷ ከግቡ አልደረሰም። ከወዳጆቿ ሳይቀር ተቃውሞ ቢገጥማትም አሁን ደግሞ ጋዛን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር ዕቅድ እንዳላት ይፋ አድርጋለች። በርካታ መሪዎቹ የተገደሉበት ሐማስ ከዚህ ጦርነት በኋላ ዕጣ ፈንታው ምን ሊሆን ይችላል?

በእስራኤል ጥቃት እየተፈተኑ በሥልጣን ላይ አንድ ዓመት የሆናቸው የኢራኑ ፕሬዝዳንት
ማሱድ ፔዜሽኪያን ሐምሌ 2024 የኢራን ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ ከአንድ ቀን በኋላ በቀጥታ ወደ ፖለቲካ እሳት ውስጥ ገብተዋል። ይህም አለመረጋጋት በሌለው በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መሪዎች ታሪክ ውስጥ ከታዩት ጅማሪዎች መካከል እጅግ አስደንጋጩ እና በቀውስ የታጀበ ነበር።

በአሜሪካ ድጋፍ የተጀመረው የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ታሪክ
በአውሮፓውያኑ መጋቢት 5/1957 ዩናይትድ ስቴትስ በወቅቱ በመሐመድ ሬዛ ፓህላቪ ከምትመራው ኢራን ጋር ለሲቪል የአውቶሚክ ኢነርጂ አጠቃቀም የትብብር ስምምነት ተፈራረመች። በ'አተምስ ፎር ፒስ' መርሃ ግብር ጥላ ስር የነበረው ይህ ስምምነት የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ለመጀመር መሠረት ጣለ። ለዋሽንግተን፣ በዚያ የቀዝቃዛ ጦርነት ወቅት ኢራን ተጨማሪ መስህብ ነበራት።
የተመለሱ ጥያቄዎች

ፎጣዎቻችን ለተለያዩ በሽታዎች ሊያጋልጡን እንደሚችሉ ያውቃሉ? እንዴት ንጽህናቸውን እንጠብቅ?
ሰውነታችንን አሊያም እጃችንን የምንደርቅባቸው ፎጣዎች ብዙ ጠቀሜታ ቢሰጡም እግረ መንገዳቸውን ረቂቅ ተህዋስያንን ከሰውነታችን ላይ ያነሳሉ።ፎጣዎቻችን ለምን ዓይነት በሽታዎች ያጋልጡናል? ፎጣዎችን ሳናጥብ ለምን ያህል ጊዜ እንጠቀምባቸዋለን? በምን ያህል ጊዜስ መታጠብ አለባቸወ?

የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ? የመንጣቱ ምክንያት ምንድን ነው?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የእድሳት ሥራው የተጠናቀቀውን የፋሲል ግንብ መርቀዋል። ባለፈው ዓመት የጥገና እድሳት እየተከናወለት በነበረበት ወቅት የግንቡ ታሪካዊ ሽሯሟ ቀለም ነጥቶ መታየቱ በርካታ መላምት እንዲሰጥ አድርጎ ነበር። የታሪካዊው ግንብ ቀለም ለዘመናት ከሚታወቅበት ተለውጦ ለምን ነጣ? የሚል ጥያቄ እንዲነሳም ምክንያት ሆኗል።በጥገና እድሳቱ በአማካሪነት እንዲሁም በጥናት የተሳተፉት አንጋፋው አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ በወቅቱ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ በማድረግ ለጉዳዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ለ20 ደቂቃ በመናፈሻዎች ውስጥ መንሸራሸር ለጤና ያለው ጥቅም
በመናፈሻ ውስጥ ወይም በጫካ ውስጥ ከተንሸራሸሩ በኋላ መረጋጋት ከተሰማዎት፣ ይህ በሃሳብዎ የፈጠሩት አይደለም ፤ ሥነ ሕይወት ነው። ከቤት ውጭ መሆን የጭንቀት ሆርሞኖችን በመቀነስ፣ የደም ግፊትን ከማቃለል አልፎ ተርፎም የሆድ እቃ ጤናን በማሻሻል በሰውነትዎ ውስጥ ሊታይ የሚችል ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። እነዚህን ጥቅሞች ለማግኘት ለሰዓታት የእግር ጉዞ ማድረግ አያስፈልግም፤ የቀንዎን 20 ደቂቃ ለዚህ ተግባር ቢያውሉ ለውጡን ያዩታል።

በተፈጥሮ ሒሳብ ሰነፍ የሆኑ ሰዎች አሉ?
ለአንዳንዶች ሒሳብ በቀላሉ የሚሠራ ሲሆን፣ ሌሎች ግን ቀላል የሚባለው ስሌት ሳይቀር ይፈትናቸዋል።ይህ ከዘረ መል ጋር እንደሚያያዝ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ነገሩ የዘረ መል ብቻ ግን አይደለም። ከሥነ ሕይወት፣ ከሥነ ልቦና እና አካባቢ ጋር ይተሳሰራል። ለመሆኑ በተፈጥሮ ሒሳብ ሰነፍ የሆኑ ሰዎች አሉ?

የኖቤል ሽልማት ምንድን ነው? እንዴት ማሸነፍ ይቻላል?
የዚህ ዓመት የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ ዛሬ መስከረም 30 2018 ዓ.ም. ይፋ ተደርጓል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሸልማት እንደሚገባቸው ሲናገሩ ቢቆዩም የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ግን ለቬንዚዌላዊቷ የተቃውሞ ፖለቲከኛ መሪ ማሪያ ኩሪና ማቻዶ ሰጥቷል። ለመሆኑ የኖቤል ሽልማት ምንድን ነው?

የያዘን ጉንፋን ይሁን ኮቪድ እንዴት መለየት እንችላለን ? እንዳይባባስ ባለሙያዎች ምን ይመክራሉ?
በጉንፋን፣በኢንፍሉዌንዛ እና በኮቪድ መካከል ያሉ የህመም ምልክቶች ይመሳሰላሉ።ሆኖም በሽታዎቹን ለመለየት የሚረዱ ጥቂት ምልክቶች አሉ።
ሌላ ዕይታ
ቢቢሲ አማርኛን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ
ከማኅደራችን

ዓለምን የሚዞረው ኢትዮጵያዊ ከዩቲዩብ ምን ያህል ያገኛል?
ከተከፈተ በዚህ ወር 20 ዓመት የሆነው የቪዲዮ ማጋሪያው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ዩቲዩብ ለብዙዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ፈጥሯል። ከእነዚህም መካከል አቤል ብርሃኑ አንዱ ነው፤ በዩቲዩብ አማካኝነት 62 ሀገራትን ዟሯል። ያልረገጠው አህጉር አንታርቲካን ብቻ ነው። ሁሉንም የአሜሪካ ግዛቶች አካሏል። ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ዩቲዩብ ላይ የቆየው አቤል ከዩቲዩብ ምንያህል ያገኛል?

ቪዲዮ,በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።

እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።

ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።

ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።

“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።

". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።

የአእምሮ ዕድገት መዛባት (ኦቲዝም) ያለባቸው መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚረዳ ጥናት ለኳታር ያቀረቡት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ
ዛሬ፣መጋቢት 24 የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው። ይህ ዕለት በዓለም ደረጃ ታስቦ እንዲውል ለተባበሩት መንግሥታት ሐሳብ ያቀረበችው ኳታር ናት። ወደዚያው ብናቀና ዶክተር ወንድወሰን ግርማን እናገኛለን። ኦቲስቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚያስችል ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።

'ዝምተኛው ገዳይ' በኢትዮጵያ
የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ የአየር ብክለት ልኬት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል። ድርጅቱ እንደሚለው 99 በመቶው የዓለም ሕዝብ የሚተነፍሰው አየር ተበክሏል። ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚዳርገው የአየር ብክለት በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያ ይናገራሉ። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ዋነኛ አየር በካዮች የትኞቹ ናቸው? መፍትሔውስ ምንድን ነው?

"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?

"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።




































































