
X /x በላቲን አልፋቤት ሀያ አራተኛው ፊደል ነው።
ግብፅኛ ጀድ | ቅድመ ሴማዊ (አልተገኘም) | የፊንቄ ጽሕፈት ሳሜክ | የግሪክ ጽሕፈት ኺ | ኤትሩስካዊ X | ላቲን X |
---|
| - |  |  |  |  |
የ«X» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ቢታስብም እስካሁን አልተገኘም። ለዚህም ምናልባት ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አንዳንድ ሊቃውንት የ"ዓምድ" ("ጀድ") ስዕል እንደ ነበር ይገምታል።
ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ለድምጹም /ስ/ አገለገለ።
በግሪክኛ ግን ከ«ሺን» የደረሰው «ሲግማ» ለ/ስ/ ስላገለገለ፣ ከሳሜክ የደረሰው ቅርጽ «Ξ» በምስራቃዊ ግሪክ አልፋቤት ለድምጹ /ክስ/ ይወከል ጀመር። ሌላ አዲስ ቅርጽ «Χ» በምሥራቅ ግሪክ አልፋቤት ለ/ኽ/ ወከለ፤ በምዕራባዊ ግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ቅርጽ ለ/ክስ/ ተጠቀመ።
በኤትሩስክኛ አልፋቤት እንዲሁም በላቲን አልፋቤት የ«X» ቅርጽ እንደ /ክስ/ ሆኖ ቆየ። በእንግሊዝኛም ደግሞ አብዛኛው ጊዜ /ክስ/ ያመልክታል። በአንዳንድ ሌሎች ቋንቋዎች ግን ልዩ ልዩ ድምጾች ሊወክል ይችላል።
በግዕዝአቡጊዳ ደግሞ «ሰ» («ሳት») የሚለው ፊደል ከሴማዊው «ሳሜክ» ስለ መጣ፣ የላቲን 'X' ዘመድ ሊባል ይችላል።
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለX የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።