
U /u በላቲን አልፋቤት 21ኛው ፊደል ነው።
ግብፅኛ ሐጅ | ቅድመ ሴማዊ ዋው | የፊንቄ ጽሕፈት ዋው | የግሪክ ጽሕፈት ኢውፕሲሎን | ኤትሩስካዊ U | ላቲን V |
---|
|  |  |  |  |  |
የ«U» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዋው» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበትር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይየግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።
በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ድምጽ እንደ ተናባቢ («ው») ሲሆን በጥንታዊግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኢው» (Υ, υ) ለማመልከት ተጠቀመ።
በኤትሩስክኛ ደግሞ «Y» ለአነባቢው «ኡ» ይወክል ነበር። በሮማይስጥ ቅርጹ ከ400 ዓም ያህል በኋላ እንደ «V» ተቀየረ፣ ይህም አንድላይ ተነባቢውን «ው» ወይም አናባቢውን «ኡ» አመለከተ።
እንዲሁም ከዘመናት በኋላ ተነባቢውን «ቭ» ድግሞ ለማመልከት ቻለ። ቅርጹም ከ«U» ጋር ይለዋወጥ ነበር። ከ1378 ዓም በታየ በአንድ አልፋቤት ለመጀመርያው ጊዜ «U» (/ኡ/) እና «V» (/ቭ/) እንደ ልዩ ልዩ ፊደላት ተቆጠሩ። በ1754 ዓም የፈረንሳይ አካደሚ በይፋ «U» እና «V» እንደ ልዩ ልዩ ፊደላት ይቆጥራቸው ጀመር።
በግዕዝአቡጊዳ ደግሞ «ወ» («ዋዌ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ዋው» ስለ መጣ፣ የላቲን 'U' ዘመድ ሊባል ይችላል። እንዲሁም የላቲንF፣V፣W፣ እናY ሁሉ ከ«ዋው» ደረሱ።
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለU የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።