
N /n በላቲን አልፋቤት አሥራ አራተኛው ፊደል ነው።
ግብፅኛ ጀ | ቅድመ ሴማዊ ኑን | የፊንቄ ጽሕፈት ኑን | የግሪክ ጽሕፈት ኑ | ኤትሩስካዊ N | ላቲን N |
|---|
|  |  |  |  |  |
የ«N» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ኑን» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የእባብ ስዕል መስለ።የግብጽኛ ተናባቢ ድምጽ ምልክቶች በሚል ጽሕፈት ለዚህ ተመሳሳይየግብጽ ሀይሮግሊፍ ለድምጹ «ጀ» ነበር፤ በሴማውያን ዘንድ ግን «ን» ሆነ። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "ኑ" (Ν ν) ደረሰ።
ከ400 ዓክልበ. ግድም በፊት፣ በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት እንዲሁም በጥንታዊ ኢታሊክ አልፋቤት የ«ም» ቅርጽም እንደ «𐌌» ይምሰል እንደ ነበር የ«ን» ቅርጽ ደግሞ እንደ «𐌍» ይጻፍ ነበር። ከዚያስ የ«𐌌» (ም) ቅርጽ እንደ ዛሬM እንደ ሆነ፣ እንዲሁም የ«𐌍» (ን) ቅርጽ የዛኔ ወደN ተቀየረ።
በአንዳንድ ቋንቋ በተለይም በእስፓንኛው አልፋቤት ተጨማሪው ፊደል «Ñ» (/ኝ/) ከN የደረሰ ነው። በእስፓንኛ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ይህ Ñ የተለየ ፊደል ሆኖ ተቆጥሯል፤ መጀመርያ ግን በጋሊስኛ ከ1220 ዓም ታውቋል።
በግዕዝአቡጊዳ ደግሞ «ነ» («ነሐስ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ኑን» ስለ መጣ፣ የላቲን 'N' ዘመድ ሊባል ይችላል።
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለN የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።