Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

H

ከውክፔዲያ
የላቲን አልፋቤት
ABCDEF
GHIJKLM
NOPQRST
UVWXYZ
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

H /hላቲን አልፋቤት ስምንተኛው ፊደል ነው። በእንግሊዝኛ የፊደሉ ስም አጠራር /ኧይች/ ቢሆንም፣ የተናባቢው ድምጽ /ህ/ ያሰማል።

ግብፅኛ
ሰፐአት
ቅድመ ሴማዊ
ሔት
የፊንቄ ጽሕፈት
ሔት
የግሪክ ጽሕፈት
ሄታ/ኤታ
ኤትሩስካዊ
H
ላቲን
H
N24

የ«H» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ሔት» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የአጥር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይየግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።

በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ሔት ድምጽ እንደ ተናባቢ («ሕ») ሲሆን በግሪክ አልፋቤት እንዲሁምሄታ ለ «ህ» ተጠቀመ። ከ450 ዓክልበ. ግድም በኋላ ግን ይህ ምልክት ትንሽ ተቀይሮ «ኤታ» (Η η) የአናባቢ ድምጽ «ኤ» ለማመልከት ይጠቅም ጀመር። ይህን ለውጥ መጀመርያ ያደረገው ባለቅኔውሲሞኒዴስ ዘኬዮስ (564-476 ዓክልበ.) እንደ ነበር በግሪክ ጽሐፊዎች ተባለ። ሆኖም በጥንታዊ ጣልያን አልፋቤቶች እንደኤትሩስካዊ አልፋቤት እና ላቲን አልፋቤት፣ «H» ተናባቢውን «ህ» በመወክል ቆየ።

ግዕዝአቡጊዳ ደግሞ «ሐ» («ሐውት») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ሔት» ስለ መጣ፣ የላቲን «H» ዘመድ ሊባል ይችላል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለH የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=H&oldid=338479» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp