Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

2 ሰኑስረት

ከውክፔዲያ

==

2 ሰኑስረት
የኻይከፐሬ  ምስል
የኻይከፐሬ ምስል
የግብጽፈርዖን
ግዛት1905-1888 ዓክልበ.?
ቀዳሚ2 አመነምሃት
ተከታይ3 ሰኑስረት
ሥርወ-መንግሥት12ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት2 አመነምሃት

==

ኻይከፐሬ፣ ፪ ሰኑስረትግብጽን በመካከለኛ መንግሥት (12ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1905 እስከ ምናልባት 1888 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛፈርዖን ነበረ። የአባቱ2 አመነምሃት ተከታይ ነበር። በተለይ የሚታወቀው በኤል-ላሑን ስላሠራው ሀረም ነው።

በኑብካውሬ ፪ አመነምሃት ዘመነ መንግሥት በ፴፫ኛው ዓመት (1907 ዓክልበ. ግድም) ልጁን 2 ሰኑስረት ከእርሱ ጋር በጋርዮሽ ወደ ዙፋኑ አስነሣው። ከዚህ ሁለት ዓመት በኋላ በ1905 ዓክልበ. ግድም ኑብካውሬ ዓረፈና ፪ ሰኑስረት ለብቻው ፈርዖን ሆነ ይመስላል።

በጠቅላላ ስንት ዓመታት ያሕል እንደ ነገሠ ተከራካሪ ነው።ማኔጦን ለኻይከፐሬ ፪ ሰኑስረት እና ለተከታዩ3 ሰኑስረት ፈንታ ለሁለቱ አንድ ስም ብቻ አለው፤ እሱምሴሶስትሪስ ሲሆን ለ፵፰ ዓመታት እንደ ገዛ ይለናል። ይሄ ሴሶስትሪስ እስከእስኩቴስ ድረስ የዘመተ በአፈ ታሪክ ይባላል። ፫ ሰኑስረት ቢያንስ በከነዓን እንደ ዘመተ ይታወቃል፤ ለ፪ ሰኑስረት ግን ምንም ዘመቻ አይታወቅም።

የቶሪኖ ቀኖና የሚባለው የፈርዖኖች ዝርዝር ሰነድ ሁለቱንም ይለያል፤ ለ፪ ሰኑስረት ፲፱ ዓመታትና ለ3 ሰኑስረት ፴ አመታት ይሠጣል። ነገር ግን ለ፪ ሰኑስረት ከ፰ኛው ዓመቱ በላይ የሆነ ዓመት ቁጥር በሥነ ቅርስ ስለማይታወቅ፤ ብዙ መምህሮች ለ፰፣ ፱ ወይም ፲ ዓመታት ብቻ እንደ ነገሠ ያምናሉ።

ሴማዊ ቤተሠቦች ከከነዓን ወደ ግብጽ ሲደርሱ በኻይከፐሬ ፪ ሰኑስረት ዘመነ መንግሥት

መጀመርያ ፫ቱ ዓመቶቹ ከአባቱ ፪ አመነምሃት በጋርዮሽ ሲሆኑ፣ ከዚህ በላይ ልጁን 3 ሰኑስረት በጋርዮሽ ወደ ዙፋኑ እንዳስነሣው የሚመለከት ማስረጃ አለ። ከዚህ ውስጥ አንድ የፓፒሩስ ሰነድ ሁለቱን ፈርዖኖች ሲጠቅስ በ፪ ሰኑስረት ፲፱ኛው ዓመትና በ፫ ሱኑስረት ፩ኛው ዓመት እንዳለ ይታስብ ነበር። ሆኖም ሌሎች መምህሮች በተቃራኒው በ፫ሰኑስረት ፲፱ኛው ዓመትና በተከታዩ በ3 አመነምሃት 1ኛው ዓመት እንደሚለው ያምናሉ።

ዩጂን ሜሪል አስተሳሰብ፣ ይህ ፈርዖንዮሴፍን የሾመው በኦሪት ዘፍጥረት ፵፩ ዘንድ ይሆናል። ይህም ደግሞ በመጽሐፈ ኩፋሌ ካለው አቆጣጠር (2164 ዓ.ዓ. ወይም 1907 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ግድም) ጋር ይስማማል። በዚህ ሥርወ መንግሥት የሌሎቹ ፈርዖኖች ጠቅላይ ሚንስትሮች ሁሉ በስም ቢታወቁ፣ የዚህ ፪ ሰኑስረት ሚኒስትር ስም ግን ከቶ አልታተምም፤ በዘፍጥረትም የዮሴፍ ግብጽኛ ስም «ጸፍናት ፐዕናህ» ሆነ።

ቀዳሚው
2 አመነምሃት
ግብፅ ፈርዖንተከታይ
3 ሰኑስረት
  • የኻይከፐሬ ሀረም በኤል-ላሑን
    የኻይከፐሬ ሀረም በኤል-ላሑን
  • በኻይከፐሬ ሴት ልጅ መቃብር የተገኘው ድሪ
    በኻይከፐሬ ሴት ልጅ መቃብር የተገኘው ድሪ
  • «ኻይከፐሬ» የሚል ካርቱሽ
    «ኻይከፐሬ» የሚል ካርቱሽ
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=2_ሰኑስረት&oldid=318876» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2026 Movatter.jp