Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

0

ከውክፔዲያ
0
ዜሮ/Zero

ዜሮ ወይንም0 ወይንምቁጥር ጽሕፈት ወቅት የባዶነት ማመላከቻ ምልክት ነው። ዜሮ በራሱም ቁጥር ሲሆንም ያንድን መለኪያ ባዶነት ያመለክታል። ለምሳሌ የባዶስብስብ አባላት ቁጥር ዜሮ ነው እንላለን።

ታሪክ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

የዜሮ ፅንሰ ሐሳብ በባቢሎኒያኖች የፈለቀ ሲሆን ይኼውም በ3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ነበር። ሆኖም ባቢሎኒያኖቹ ዜሮን እኛ እንደምንጠቀምበት ሳይሆን እንደ ቦታ ያዢ ምልክት ነበር የጠቀሙበት። ለምሳሌ 304፣ ወይንም 450 ሲጽፉ፣ 0 እዚህ ላይ የቁጥር አለመኖርንና ቦታ መያዝን ብቻ ያመላክታል።

ዜሮን እኛ በምንጠቀምበት መልኩ የተጠቀሙትህንዶች ሲሆኑ ይሄውም ቢያንስ ከ620 ዓ.ም. ጀምሮ ነበረ።[1] ለህንዶች፣ ዜሮ ቦታ መያዣ ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ እራሱን የቻለቁጥር ሲሆን ለስሌት የሚረዳ ነበር። በህንዶች ዘንድ 0 ለመደመር፣ ለመቀነስ፣ ለማካፈልና ለማባዛት ግልጋሎት ይውል ነበር።

768 ዓም ጀምሮአረቦች ከህንዶች የዚህን ቁጥር ጥበብ በመቅሰም ለአዲሱ ቁጥርስፍርصفر የሚል ስያሜ ሰጡት። ትርጓሜውምባዶ ማለት ነበር። የአረብ ሊቃውንት ከአውሮፓ ሊቃውንት በነዚህ ፪ መቶ አመታት በዜሮ (0) ጥቅም ቅድምትነታቸው ምክንያት፣ በሥነ ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሳይንስ ዘርፎች ሥነ ቁጥሮች በመቀለላቸው በኩል፣ ለጊዜው የአረብ አለም ሊቃውንት በይበልጥ ለመግፋት ቻሉ።

ከዚያ ቁጥሩ መጀመርያ በአውሮፓዊ መጽሐፍ የተጠቀሰው በ968 ዓም ነበር። ከአረቦቹ ይህን ቁጥር የቀሰመውጣሊያኑፊቦናቺ «ስፍር» የሚለውን ወደዜፊሮ በመቀየር የቁጥሩ ጥቅም በተለይ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. አውሮጳ እንዲስፋፋ ሆነ። በኋላም በእንግሊዝኛ «ዜፊሮ» ወደ «ዜሮ» ተለውጦ ስሙ በዚህ ረጋ።

ዜሮና ሒሳብ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

የዜሮ ጠባዮች

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
  • መደመር:x + 0 = 0 +x =x. ዜሮን ሌላ ቁጥር ላይ መደመር ያን ቁጥር አይለውጥም
  • መቀነስ:x − 0 =x and 0 −x = −x.
  • ማባዛት:x · 0 = 0 ·x = 0.
  • ማካፈል: 0|x = 0,x እዚህ ላይ ዜሮ ያልሆነ ቁጥር ነው። በአንጻሩx|0ያልተተርጎመ ነው።
  • ንሴት:x0 =x/x = 1, ይህ የማይሰራውx = 0 ሲሆን ብቻ ነው። በተጨማሪ ለማንኛው እውን ቁጥርx, 0x = 0.

ነጥቦች

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
  1. ^2010 ዓም፣ ተመርማሪዎች በ«ካርቦን ዝመና» ዘዴ በኩል ዜሮ የሚጠቀምበት አንድ ሰነድ ከ200-400 ዓ.ም. እንደ ሆነ አሳወቁ። «ካርቦን ዝመና» ግን እጅግ አጠያያቂ ዘዴ ነው።
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=0&oldid=383322» የተወሰደ
መደብ:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp