Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ጋና

ከውክፔዲያ

Republic of Ghana
የጋና ሬፑብሊክ

የጋና ሰንደቅ ዓላማየጋና አርማ
ሰንደቅ ዓላማአርማ
ብሔራዊ መዝሙር: God Bless Our Homeland Ghana

የጋናመገኛ
የጋናመገኛ
ዋና ከተማአክራ
ብሔራዊ ቋንቋዎችእንግሊዝኛ (መደበኛ)
መንግሥት
{{{
ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
 
ናና አኩፎ-አዶ
ማዏምሙዱ ባዉሚዓ
ዋና ቀናት
የካቲት ፳፯ ቀን፲፱፻፵፱ ዓ.ም.
(6ማርች 1957 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት ከብሪታንያ ታወጀ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
238,535 (80ኛ)
4.61
የሕዝብ ብዛት
የ2014 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2010 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
27,043,093 (46ኛ)
24,200,000
ገንዘብሴዲ
ሰዓት ክልልUTC +0
የስልክ መግቢያ+233
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን.gh

ጋናአፍሪካአትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት።

የጋና ስራ ቋንቋእንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይምትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያአሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ።

ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ።

የጋና ዋና ምርቶችካካዎዘይትአልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል።

እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤጐርጠብየስኳር ድንችባቄላበቆሎኦቾሎኒባሚያሩዝ ይሠራል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለጋና የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።


አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
Map indicating Western Africaምዕራብ አፍሪቃ
Map indicating Northern Africaስሜን አፍሪቃ
Map indicating Central Africaመካከለኛ አፍሪቃ
Map indicating Eastern Africaምሥራቅ አፍሪቃ
Map indicating Southern Africaደቡባዊ አፍሪቃ
 በጥገኝነት፡
 ዕውቅና ያልተሰጠ፡
1 ኹኔታው ያልተረጋገጠ ነው። 2 ግዛቱ በከፊል በእስያ ነው። 
(ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍመሠረትወይምመዋቅርነው። እርስዎሊያስፋፉት ይችላሉ!)
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ጋና&oldid=377238» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp