Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ዩጋንዳ

ከውክፔዲያ

Republic of Uganda
የዩጋንዳ ሬፑብሊክ

የዩጋንዳ ሰንደቅ ዓላማየዩጋንዳ አርማ
ሰንደቅ ዓላማአርማ
የዩጋንዳመገኛ
የዩጋንዳመገኛ
ዋና ከተማካምፓላ
ብሔራዊ ቋንቋዎችእንግሊዝኛስዋሂሊ
መንግሥት
{{{ፕሬዚዳንት
 
ዮወሪ ሙሰቬኒ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
236,040 (81ኛ)
ገንዘብሺሊንግ
ሰዓት ክልልUTC +3
የስልክ መግቢያ+256

ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይምዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያደቡብ ሱዳንኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክሩዋንዳ እናታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው።

ታሪክ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመንችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች።

1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትርሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ.ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንትዮወሪ ሙሴቪኒ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው።

ፖለቲካ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
ዮወሪ ሙሴቪኒ

ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትርአፖሎ ሲባምቢ ናቸው።

መልከዓ-ምድር

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥምቪክቶሪያ ሐይቅአልበርት ሐይቅክዮጋ ሐይቅ እናኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህምካምፓላንናእንትቤን ያጠቃልላል።

ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት።

ኤኮኖሚ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እናነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል።

የሕዝብ እስታቲስቲክስ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላእንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል።ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው።

ግንኙነት

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

ስልክ፦

  • መስመሮች - 54,074 (1998 እ.ኤ.አ.)
  • የእጅ ስልኮች - 9,000 (1998 እ.ኤ.አ.)

ራዲዮ

  • ማሰራጫ ስቴሽኖች - AM 19, FM 4
  • ራዲዮኖች - 2.6 ሚሊዮን (1997 እ.ኤ.አ.)

ቴሌቪዥን

  • ማሰራጫ ስቴሽኖች - 8
  • ቴሌቪዥኖች - 315,000 (1997 እ.ኤ.አ.)

ኢንተርኔት

  • የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች - 3 (1999 እ.ኤ.አ.)
  • የኢንተርኔት ሀገር ኮድ - .ug

ትምህርት

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል።የትምህርት ስርዐቱ ከ1960ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል።

ትራንስፖርት

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
  • አጠቃላይ የባቡር መንገድ - 1,241 ኪ.ሜ.
  • አጠቃላይ መንገድ ርዝመት - 27,000 ኪ.ሜ.
  • ሄሊኮፕተር ማረፊያ - 2

አውሮፕላን ማረፊያ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]


አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
Map indicating Western Africaምዕራብ አፍሪቃ
Map indicating Northern Africaስሜን አፍሪቃ
Map indicating Central Africaመካከለኛ አፍሪቃ
Map indicating Eastern Africaምሥራቅ አፍሪቃ
Map indicating Southern Africaደቡባዊ አፍሪቃ
 በጥገኝነት፡
 ዕውቅና ያልተሰጠ፡
1 ኹኔታው ያልተረጋገጠ ነው። 2 ግዛቱ በከፊል በእስያ ነው። 
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ዩጋንዳ&oldid=340665» የተወሰደ
መደብ:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp