?የዝባድ በሬ |
---|

|
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ |
---|
|

የዝባድ በሬ በተፈጥሮ (ቀይ) እና ሰዎች አስገብተው (ሰማያዊ) የሚገኝባቸው ቦታዎች |
የዝባድ በሬ (ሮማይስጥ፦Ovibos moschatus) በአርክቲክ ዙሪያ የሚገኝየቶራ አስተኔ አባል ነው።
የዝባድ በሬ መንጋ መከላከያ ሠልፍየዝባድ በሬ ወንድ ብርቱ ጠረን የሚሰጡ እጢዎች አሉት። ይህ ሴቶችን ለማዳራት ነው። ወንዶችም ሴቶችም ሁለት ረጅም፣ ጥምዝ ቀንዶች በራሳቸው ላይ አሏቸው። ወንዶችም ከደመነፍስ የተነሣ እርስ በርስ ለሴቶችም ሆነ ለሣር ቡጢ ያደርጋሉ።
የዝባድ በሬ የሚበላውሣር፣በለሴት፣ሳርንስት፣የአርክቲክ አኻያ ቊጥቋጥ፣ ወዘተ. ነው።
ዝባድ በሬን የሚበላው ነጣቂ በተለይየአርክቲክ ተኲላ ነው። አልፎ አልፎየዋልታ ድብ ወይምቡናማ ድብ ድካሙን ይነጥቃል። በሚበዙበት ጊዜ፣የሰው ልጅ ደግሞ ለሥጋው ያድናቸዋል።
በመንጋው ምናልባት 8-24 በሬዎች ይሆናሉ። ጥቃት ቢደርስባቸው፣ ለመከላከያ ፊታቸውን ወደ ውጭ አድርገው በክብ ነገር ቁመው የቀለበት ቅርጽ ይሠራሉ።
የተፈጥሮ መኖሪያቸው በስሜንግሪንላንድና በስሜንካናዳ ሲሆን፣ ከዚህ በላይ የሰው ልጆች ወደአላስካ፣ስካንዲናቪያናሳይቤሪያ አስገብተዋቸዋል። አንዳንዴ ይህ የሚደረግ ለማደኑ እንዲበዙ ነው። በመላው ዓለም በጠቅላላ አሁን ምናልባት 125 ሺህ ያህል ዝባድ በሬዎች ይኖራሉ።
«ቂቪዩት» የተባለ ከፍተኛ ጥራት ያለውንሱፍ ይሰጣሉ። አልፎ አልፎ ብቻ የዝባድ በሬዎች ለሱፍ፣ ለወተትና ለሥጋ ለማዳ እንስሶች ተደርገዋል።