፫ቱን የሕይወት ዓይነቶች እሚያሳይ ምስልየአንድ ሕይወት ያለው ማህብረሰብ የዘር ውርስ ባህሪይ ከትውልድ ወደትውልድ እየተቀየረ መሄዱዝግመተ ለውጥ ይባላል።ቻርለስ ዳርዊን ይህን ኩነት በማስተዋልና በሳይንሳዊአመክንዮ አሰደግፎ በመተንተኑ የመጀመሪያው ሰው ነው። ዳርዊን በተጨማሪየተፈጥሮ ምርጫ ባለውኅልዮቱ ሕይወት ያላቸው ማህበረሰቦች ዝግመተ ለውጥ እሚያካሂዱት ምንም እንኳ በዘፈቀደ ስህተት እየፈጸሙ ቢሆንም፣ ተፈጥሮ እራሷ በምትፈጥረው መሰናክሎች እኒህን መሰናክሎች አልፈው የሚሄዱትን በመምረጧ ነው። ዳርዊን የተፈጥሮ ምርጫን አስተሳሰብ ከ፫ የሚታዩ ነገሮች አንጥሮ ነበር ያወጣው፦ ፩) እንስሳትም ሆነ እጽዋት ወደፊት ሊኖር ከሚችሉ ዘሮች በላይ አተረፍርፈው ነው እሚራቡት ፪) ሕይወት ያላቸው እያንዳንዳቸው ነገሮች ሁልጊዜ የተለያየ ጸባይ ነው ያላቸው፣ ስለሆነም እያንዳንዳንቸው በቀጣይ የመኖር ዕድላቸው የተለያየ ነው ፫) ስለሆነም የአንድ ማህበረሰብ አባላት ሲሞቱ፣ የሚገላቸውን ነገር ጠንክረው እሚቋቋሙት ግለሰቦች ብቻ በሕይወት ቆይተው ወደፊት መራባች ይችላሉ። ስለሆነም ቀስ በቀስ እነዚህ በህይወት ያሉ፣ በህይወት የሌሉትን አይነቶች እየተኩ ይሄዳሉ።
በ፳ኛው ክፍለ ዘመንጄኔቲክስ (ሥነ በራሂ) እና ዝግመተ ለውጥ ተዋህደውማህበረሰባዊ ጄኔትክስ እሚባለውን ጥናት ለመፍጠር ችለዋል። አንድ ማህበርሰብ ለየት ያለ ግለሰቦችን ለመፍጠር ከሚያስችሉት መንገዶች አንዱሙቴሽን የተባለው ሂደት ሲሆን፣ ሙቴሽን እሚፈጠረው የዚያ ግለሰብዲ ኤን ኤ ከወላጆች ሲወረስ በሚደረግ ስህተት (ወይም እቅድ) ነው።
ባለሙያ ንድፍ የተባለው ትምህርት ከሥነ በራሂ ጥናት የምንማረው መረጃ ሁሉ በፈጣሪው እቅድ እንደ ሆነ ለመግለጽ ይሞክራል። በተለይ በመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ ፩፡፳፮ መሠረት በመሰለ ስሜት፣ «ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፣ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፣ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ» ይላል።
የሰው ልጅሐብለ በራሂ (ክሮሞሶም) ከሕያዋን ሁሉ በተለይ ለቺምፓንዚጦጣ ሐብለ በራሂ ዝምድና እንዳለው ተገልጿል። ቺምፓንዚ ግን እንደሰው ልጅ ሳይሆን ሌሎችን እንስሳት ወይምአትክልት ለማዳ ለማድረግ እንዳልተዘጋጀ ግልጽ ነው። በዝርዝሩ ስንመልክተው፣ የሰው ልጅ ሐብለ በራሂና የቺምፓንዚ ሐብለ በራሂ የሚለያዩ በአንዱ እሱም በሰዎች፪ኛው ሐብለ በራሂ ሲሆን፣ በቺምፓንዚ ግን በዚያው ሥፍራ ሁለት ልዩ ልዩ አጫጭር ሐብለ በራሂዎች አሉዋቸው። ከዚህ መረጃ የቺምፓንዚ ሐብለ በራሂ ወደ ሰው ልጅ ሐብለ በራሂ ለመቀይር፣ እነዚህ ሁለት ልዩ ልዩ አጫጭር ሐብለ በራሂዎች አንድላይ በትክክል በፍጹምነት በጥንቃቄ በእቅድ ማጋጥምና ማዋኸድ አስፈለገ። ይህ ድርጊት ተዓምር መሆን ነበረበትና ለ«ባለምያ ንድፍ» እንደ ማስረጃ ይቆጠራል። ስለዚህ የሰው ልጅ ክሮሞሶም በአንድ ትውልድ መከሠት ነበረበት እንጂ በብዙ ሚሊዮን ዘመን ዝግታዊ ሂደት የሚለወጥ አይመስልም፤ የሰው ልጅ በራሂ አራያ ከቺምፓንዚ በራሂ አራያ የተለወጠበትም ዘመን ከ6000 ዓመታት በፊት አይሆንም ይላል።