Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ኬንያ

ከውክፔዲያ

የኬንያ ሪፐብሊክ
Jamhuri ya Kenya(ስዋሂሊ)
(ጃምሁሪ ያ ኬኛ)

የኬንያ ሰንደቅ ዓላማየኬንያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማአርማ
ብሔራዊ መዝሙር:  «ኤ ሙንጉ ንጉቩ ዬቱ»(ስዋሂሊ)
የኬንያመገኛ
የኬንያመገኛ
ኬንያ በአረንጓዴ ቀለም
ዋና ከተማናይሮቢ
ብሔራዊ ቋንቋዎችስዋሂሊ እናእንግሊዝኛ
መንግሥት
{{{
ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ኡሁሩ ኬንያታ
ዊልየም ሩቶ
ዋና ቀናት
ታኅሣሥ ፪ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. (ዲሴምበር 12, 1963 እ.ኤ.አ.)
ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. (ዲሴምበር 12, 1964 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት ከብሪታንያ

ሪፐብሊክ ታወጀ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
580,367 (47ኛ)
2.3
የሕዝብ ብዛት
የ2021 እ.ኤ.አ. ግምት
የነሐሴ 2019 ዓ.ም. ቆጠራ
 
54,985,698 (29ኛ)
47,564,296
ገንዘብየኬንያ ሺሊንግ
ሰዓት ክልልUTC +3
የስልክ መግቢያ+254
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን.ke

የኬንያ ሪፐብሊክ በምስራቅአፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በሰሜን ከኢትዮጵያ፣ በሰሜን-ምስራቅ ከሶማሊያ፣ በደቡብ ከታንዛኒያ፣ በምስራቅ ከዩጋንዳ፣ በስሜን-ምዕራብ ከደቡብ ሱዳን፣ በደቡብ-ምስራቅ ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር ድንበር ትጋራለች።

አውሮፓውያን አካባቢውን ማሰስ የጀመሩት ከ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲሆንየብሪታንያ መንግሥትየምሥራቅ አፍሪካ ፕሮቴክቶሬትን በ1895 እ.ኤ.አ. አቋቁሟል። ይህ ፕሮቴክቶሬት በ1920 እ.ኤ.አ.የኬንያ ግዛት ተብሎ ተሰይሟል። ነፃ የኬንያ ሪፐብሊክ በዲሴምበር 1963 እ.ኤ.አ. ታወጀ።

የኬንያ ስም የመጣው በአፍሪካ በከፍታ ሁለተኛ ከሆነው ከደብረ ኬንያ ተራራ ነው። በዚሁ ተራራ ዙሪያ የሚኖሩት ነገዶች ስሙን «ኪኛ» (በካምባኛ)፣ «ኪሪማራ» (በአመሩኛ)፣ «ኪሬኛ» (በኤምቡኛ)፣ «ኪሪኛጋ» (በኪኩዩ)፣ ወይም «ኬሪ» (በመዓሳይኛ) ይሉታል። የነዚህ ስሞች ሁሉ ትርጉሞች «ቡራቡሬ» ሲሆኑ ይህም ደግሞ «ሰጎን» ማለት ነው፤አመዳይ ያለበት የተራራው ጫፍ ለተመልካች ቡራቡሬ ወንድ ሰጎንን ያሳስባልና።

በኦገስት 2010 እ.ኤ.አ. በተካሄደ ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት ከብሪታንያ የተወረሰው ሕገ መንግሥት በአዲስ ሕገ መንግሥት ተለውጧል። በአሁኑ ጊዜ ኬንያ በ፵፯ ካውንቲዎች (የአስተዳደር ክፍሎች) ተዋቅራለች። እነዚህ ካውንቲዎች በሕዝብ በተመረጡ ሰዎች የሚስተዳደሩ ሲሆን በናይሮቢ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግሥት በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ።

የኬንያ ዋና ከተማ እና ትልቋ ከተማናይሮቢ ናት። የኬንያ ኢኮኖሚ በምሥራቅና መካከለኛው አፍሪቃ በጂ.ዲ.ፒ. (GDP) ትልቁ ነው።ግብርና በአገሪቱ ትልቅ የሥራ ዘርፍ ሲሆን ከኤክስፖርቶች መካከልሻይቡና እና ከቅርብ ጊዜ ጀምሮአበባዎች ይገኛሉ። እንዲሁምቱሪስምፔትሮሊየም አቢይ ዘርፎች ናቸው።


አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
Map indicating Western Africaምዕራብ አፍሪቃ
Map indicating Northern Africaስሜን አፍሪቃ
Map indicating Central Africaመካከለኛ አፍሪቃ
Map indicating Eastern Africaምሥራቅ አፍሪቃ
Map indicating Southern Africaደቡባዊ አፍሪቃ
 በጥገኝነት፡
 ዕውቅና ያልተሰጠ፡
1 ኹኔታው ያልተረጋገጠ ነው። 2 ግዛቱ በከፊል በእስያ ነው። 
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ኬንያ&oldid=372184» የተወሰደ
መደብ:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp