Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

አንጎላ

ከውክፔዲያ

የአንጎላ ሪፐብሊክ
República de Angola(ፖርቱጊዝ)

የአንጎላ ሰንደቅ ዓላማየአንጎላ አርማ
ሰንደቅ ዓላማአርማ
ብሔራዊ መዝሙር: ወደፊት አንጎላ!
(ፖርቱጊዝ) Angola Avante!
የአንጎላመገኛ
የአንጎላመገኛ
አንጎላ በሰማያዊ ቀለም
ዋና ከተማሏንዳ
ብሔራዊ ቋንቋዎችፖርቱጊዝ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
 
João Lourenço
ዋና ቀናት
ኅዳር ፩ ቀን ፲፱፻፷፰
(ኖቬምበር 11, 1975 እ.ኤ.ኣ.)
 
João Lourençoየመሬት_ስፋት = 1,246,700
የሕዝብ ብዛት
የ2014 እ.ኤ.አ. ግምት
የ ቆጠራ
 
25,789,024 (50ኛ)
5,646,177
ገንዘብክዋንዛ
ሰዓት ክልልUTC +1
የስልክ መግቢያ+244
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን.ao

አንጎላ፣ በይፋየአንጎላ ሪፑብሊክ (ፖርቱጊዝ:República de Angolaኪኮንጎ:Repubilika ya Ngola) በደቡብ-ምዕራብአፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከናሚቢያ ፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ እና ከዛምቢያ ጋር ድንበር ትጋራላች። በምዕራብ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ትገናኛለች። የፖርቹጋል ቅኝ-ተገዥ ነበረች። ነዳጅ እና አልማዝ ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የሚመደቡ ናቸው። የአንጎላ የሕግ-አስፈጻሚ ፕሬዝዳንቱን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የሚኒስትሮች ካውንስሉን ያጠቃልላል። ሁሉም ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የሚኒስተሮች ካውንስሉን ሲሰሩ በየጊዜው እየተሰበሰቡ ስለተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣሉ። የአስራ ስምንቱ ክልሎች መሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚመረጡት። በ1992 እ.ኤ.ኣ. የወጣ ሕገ-መንግስት የመንግስቱን አወቃቀር እና የዜጎችን መብትና ግዴታ ይዘረዝራል። ፕሬዝዳንቱ መንግሥቱ በ2006 እ.ኤ.ኣ. ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ እነዳለው ገልጸዋል። ይህ ምርጫ ከ1992 አ.ኤ.ኣ. በኋላ የመጀመሪያው ምርጫ ነው የሚሆነው። አንጎላ ውስጥ ሶስት ዋና ብሔረሰቦች ይገኛሉ። ኦቪምቡንዱ 37% ፣ ኪምቡንዱ 25% ፣ እና ባኮንጎ 13%። ሌሎች ብሔረሰቦች ቾክዌ (ሉንዳ)፣ ጋንጉዌላ፣ ንሀኔካ-ሁምቤ፣ አምቦ፣ ሄሬሮ፣ እና ዢንዱንጋን ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም ክልሶች (አውሮፓና አፍሪካዊ) 2% ይሆናሉ። ፖርቱጋሎች አንጎላዊ ካልሆኑ ሰዎች ብዙዎቹ ናቸው።

ታሪክ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
ንግሥት ንዚንጋ ከሏንዳ አስተዳዳሪ ጋር የሰላም ስምምነት ስታደርግ፣ 1657 እ.ኤ.አ.

በአንጎላ መጀመሪያ የሠፈሩት የኮይሳን ሰዎች ነበሩ። በባንቱ ፍልሰቶች ጊዜ እነዚህ ሰዎች ወደ ደቡብ አንጎላ ሄዱ። በ1483 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋሎች በኮንጎ ወንዝ አጠገብ ሠፈሩ። በ1575 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋልካቢንዳ ጋር በባሪያ ንግድ ላይ ያቶከረ ግዛት መሠረተች። በ16ኛው ክፍለ ዘመን፣ ፖርቱጋል የአንጎላ የባህር ጠረፍን ተቆጣጠረች። በተለያዩ ውሎችና ጦርነቶች የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት አንጎላ ተስፋፋ። የፖርቱጋል መመለሻ ጦርነትን ምክኒያት በማድረግ የደች ሪፐብሊክ ሏንዳን ከ1641 እስከ 1648 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ተቆጣጠረች።

የቅኝ ግዛት ጊዜ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠረች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ.ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ፳ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተቆጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር።

ነፃነትና የእርስ በርስ ጦርነት

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

አንጎላ ነጻነቷን በኅዳር ፲፱፻፷፰ ከተቀዳጀች በኋላ ግን ለብዙ አሥርተ ዓመታት የሚቀጥልየእርስ በርስ ጦርነት ገጠማት። ይህ ውጊያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞትና ስደት አብቅቷል። ከአልቮር ስምምነት በኋላ ሶስቱ ትልቅ የትግል ግንባሮች የሽግግር መንግሥትን ለማቋቋም በጃኑዋሪ 1975 እ.ኤ.አ. ተስማሙ። ነገር ግን በሁለት ወራት ውስጥ እነዚህ ግንባሮች ወደ ውጊያ ተመልሰው አገሯ ወደ ክፍፍል እያመራች ነበር። በዚህ ወቅትየቀዝቃዛው ጦርነት ኃያል አገራት የነበሩትየሶቭየት ሕብረትአሜሪካ አንዱን ወይም ሌላውን ወገን ደግፈው ወደ ጦርነቱ ገብተዋል። ሌሎችም እንደፖርቱጋልብራዚልደቡብ አፍሪካኩባ የመሳሰሉት ሀገራትም ከማገዝ ወደ ኋላ አላሉም።

ፖለቲካ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

የአንጎላ የሕግ አስፈፃሚ አካል ፕሬዝዳንቱን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱንና የሚኒስትሮች ምክር ቤቱን ያጠቃልላል። ለብዙ ዓመታት አብዛኛው ሥልጣን በፕሬዝዳንቱ እጅ ነው ያተኮረው። የ፲፰ቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት።

የ1992 እ.ኤ.አ. ሕገ መንግሥት የመንግሥቱን አወቃቀርና የዜጎችን መብቶችና ግዴታዎች ይዘረዝራል። የሀገሩ ሕግ ተርጓሚ አካል የፖርቱጋል ሥርዓትን ይከተላል።

ጦር ኃይል

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

የአንጎላ ጦር ኃይሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ሲሆኑ በሦስት ይከፈላሉ። እነዚህም ምድር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና አየር ኃይል ናቸው። የሀገሩ ጠቅላላ ሠራዊት ፻፲ ሺህ ይሆናል። የጦር ኃይሉ ንብረቶች መካከል በሩሲያ የተሰሩ ተዋጊ፣ ቦምብ ጣይና አጓጓዥ አውሮፕላኖች ይገኛሉ። አንዳንድ የጦር ኃይሉ ክፍሎች በኮንጎ ኪንሻሳኮንጎ ብራዛቪል ተመድበዋል።

መልከዕ-ምድር

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

አንጎላ፣ በ1,246,620 ካሬ ኪ.ሜ. ከኒጄር ቀጥላ ከዓለም 23ኛው ትልቅ አገር ናት። በስፋት ከማሊ ጋር ትነጻጸራለች። የአሜሪካቴክሳስ ክፍላገርን ሁለት ዕጥፍ ታክላለች። አንጎላ ከደቡብ በናሚቢያ፣ ከምሥራቅ በዛምቢያ፣ ከሰሜን-ምሥራቅ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች።

የአንጎላ አማካይ የባህድ ዳር የአየር ሁኔታ በክረምት 16° ሴንቲግሬድና በበጋ 21° ሴንቲግሬድ ነው። አንጎላ ሁለት ወቅቶች አሏት። እነዚህም ደረቅና ዝናባማ ናቸው።

የአመራር ክልሎች

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
የአንጎላ ክልሎች በቁጥር ተሰይመው
ክልልየሕዝብ ብዛትየመሬት ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.)ዋና ከተማ
1.ቤንጎ450,00033,016ካክሲቶ
2.ቤንጉዌላ600,0001,788ቤንጉዌላ
3.ባኤ800,00070,314ኩዊቶ
4.ካቢንዳ300,0007,283
5.ኩዋንዶ ኩባንጎ140,000199,049ሜኖንጉዌ
6.ኩዋንዛ ኖርቴ400,00024,110ንዳላንታንዶ
7.ኩዋንዛ ሱል600,00055,660ሱምቤ
8.ኩኔኔ200,00087,342ኦንዲጂቫ
9.ሁዋምቦ1,000,00034,270ሁዋምቦ
10.ሁኺላ700,00075,002ሉባንጎ
11.ሉዋንዳ3,000,0002,257ሉዋንዳ
12.ሉንዳ ኖርቴ103,000103,000ሉካፓ
13.ሉንዳ ሱል125,00077,637ሳውሪሞ
14.ማላንጄ850,00097,602ማላንጄ
15.ሞክሲኮ230,000223,023ሉኼና
16.ናሚቤ60,00058,137ናሚቤ
17.ኡዊጂ800,00058,698ኡዊጂ
18.ዛየር600,00040,130ምባንዛ ኮንጎ

መጓጓዣ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

የአንጎላ መጓጓዣዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦

  • በአንድ ላይ ርዝመታቸው 2,761 ኪ.ሜ. የሆኑ ሦስት የባቡር መንገዶች
  • 76,626 ኪ.ሜ. አውራ ጎዳና ከዚህም ውስጥ 19,156 ኪ.ሜ. አስፋልት
  • 1,295 ኪ.ሜ. የውሃ መንገድ
  • ስምንት ትልቅ ወደቦች
  • 243 የአውሮፕላን ማረፊያዎች ከነዚህም 32ቱ የአስፋልት መንደርደሪያ ያላቸው

አንጎላ የሰፋ የመጓጓዛ አውታር ቢኖራትም በጊዜ ማለፍና ጦርነት ምክንያት መንገዶች አስፈላጊ ጥገኛ አልተደረገባቸውም። በአንዳንድ ቦታዎች አሽከርካሪዎች መጥፎ ቦታዎችን ለማለፍ ሲሉ ከመንገድ ውጭ ይነዳሉ። እንደዚህ ከማድረግ በፊት ግን በመንገድ ዳር ያሉ በመሬት ውስጥ ስለተቀበሩ ፈንጂዎች የሚያስጠነቅቁ ምልክቶችን ማስተዋል ያስፈልጋል።

ኢኮኖሚ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

የአንጎላ ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ አሳይቷል። የሩብ ምእተ ዓመት ጦርነት ያሳደረበት ተጽእኖን አልፎ ዛሬ በዓለም ውስጥ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። በ2004 እ.ኤ.አ. የቻይናኤክሲምባንክ ፪ ቢሊዮን ብር ለአንጎላ አበድሯል። ይህ ገንዘብ እንደ መንገዶች ያሉትን የአንጎላ መሠረታዊ ተቋሞች ለማሻሻል የሚውል ነው።

ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት በ2008 እ.ኤ.አ. እንደዘገበው ነዳጅና ዕንቁ የአንጎላ ዋና ኤክስፖርቶችና የገቢ ምንጮች ናቸው።[1]

ማመዛገቢያ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
  1. (እንግሊዝኛ)ዘ ኢኮኖሚስት (The Economist). August 30, 2008 እ.ኤ.አ. ዕትም. የአሜሪካ ዕትም. ገጽ 46. Article on Angola, "marches toward riches and democracy?".


አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
Map indicating Western Africaምዕራብ አፍሪቃ
Map indicating Northern Africaስሜን አፍሪቃ
Map indicating Central Africaመካከለኛ አፍሪቃ
Map indicating Eastern Africaምሥራቅ አፍሪቃ
Map indicating Southern Africaደቡባዊ አፍሪቃ
 በጥገኝነት፡
 ዕውቅና ያልተሰጠ፡
1 ኹኔታው ያልተረጋገጠ ነው። 2 ግዛቱ በከፊል በእስያ ነው። 
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=አንጎላ&oldid=348425» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp