| አተም |
|---|
 |
| የሂሊየም አተም ሐምራዊውኑክሊየስን፣
ጥቁሩ ጭጋግ የኤሌክትሮን ደመናን፣ እና
ጥቁሩ አሞሌ መስመር (10−10 m or 100 pm)ን ይወክላሉ። |
| ክፍፍሎች |
|---|
| አቶም የኬሚካልንጥር ታናሹ ክፍልፋይ ነው |
|
|
| ጸባዮች |
|---|
|
|
አቶም ወይምአተም ሁሉም ቁስ የተገነባበት መሰረታዊእኑስ ነው። እንደግዝፈታቸው፣ መጠናቸው የተያየ ስም ያላቸው ብዙ አይነት አተሞች አሉ። እነዚህ የተያዩ አይነት አተሞችየኬሚካል ንጥር ይባላሉ። ለምሳሌወርቅ አንዱ የንጥር አይነት ነው።
አተሞች ለአይን እማይታዩ፣ በጣም ደቃቅ ቢሆኑም ትክክለኛ መጠናቸው ግን ከንጥር ንጥር ይለያያል። በአጠቃላይ መልኩ አተሞች ከ 0.1 እስከ 0.5ናኖ ሜትር ስፋት ሊኖራቸው ይችላል
አብላጫውን ጊዜ አተሞች ብቻቸውን አይገኙም። ይልቁኑ አንዱ አቶም ከሌላ አቶም ጋር በመጋጠምሞልኪዩል የተሰኘውን እኑስ ይፈጥራሉ። ለምሳሌ ሁለት የሃይድሮጅን እና አንድ የኦክሲጅን አተሞች ሲጋጠሙ የውሃ ሞልኪዩልን ይፈጥራሉ።
አተሞች በራሳቸው ከ3 አንስተኛ እኑሶች የተሰሩ ናቸው። እነዚህምኤሌክትሮን፣ፕሮቶን እናኒውትሮን ይባላሉ። ፕሮቶኖችና ኒውትሮኖች አንድ ላይ ሆነው በአቶሙ መሃል ተጠጋግተው ሲቀመጡ የአተሙን ኒኩሊየስ ይፈጥራሉ። ኤሌክትሮኖች በበኩላቸው ይህን ኒኩሊየስ በደመና መልክ ከበው ይገኛሉ። ኤሌክትሮኖች ምንም እንኳ ኒኩሊየሱን እየከበቡ ቢሽከረከሩም ከኒኩሊየሱ በረው እንዳይጠፉ የኤሌክትሮመግነጢስጉልበት አዋዶ ይይዛቸዋል።
በአተም ውስጥ የሚገኙት የፕሮቶን፣ ኒውትሮንና እና ኤሌክትሮን ብዛቶች ያ አተም ምንንጥር እንደሆነ ይወስናል። ለምሳሌ አንድ አቶም 1 ፕሮቶን፣ 0 ኒውትሮን እና 1 ኤሌክትሮን ካለውሃይድሮጅን ይሆናል፣ በአንጻሩ 16 ፕሮቶን፣ 16 ኒውትሮን እና 16 ኤሌክትሮን ካለውድኝ (ሰልፈር) ይሆናል ማለት ነው።
አተሞች እርስ በርሳቸው ሳይጋፉ ሰፋ ብለው ሲቀመጡጋዝ ወይንምአየር ይሆናሉ። በተቃራኒ፣ ጭፍግ ብለው አንድ ቦታ ላይ ሲገኙ እና መንቀሳቀስ እሚችሉ በመንቀጥቀጥ ከሆነጠጣር ነገር ይሆናሉ።
እቶን የአቶም እሳት በአቶም ፉዝዮን ወይም አቶምን በመክፈል የሚገኝ እጂ-ትልቅ ኃይል ነው።