አቫሪስ (ግሪክኛ፦ Αυαρις /አዋሪስ/፣ግብጽኛ፦ ሑት-ዋረት፣ ሐዋረት) ጥንታዊ የግብጽ ከተማ ነበረ።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ «ጣኔዎስ» ወይም «ጣይናስ» በአብርሃም ዘመን ከኬብሮን 7 ዓመታት በኋላ መሠራቱን ሲያመለከት (ኩፋሌ 11:23፣ኦሪት ዘኊልቊ 13፡22)፣ የዚሁ አቫሪስ ሥፍራ ማለት ሳይሆን አይቀርም። በሂክሶስ ዘመን የሂክሶስ ዋና ከተማ ሆነ። በኋላ (1548 ዓክልበ. ግድም) የግብጽ ኗሪ18ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን1 አህሞስ አቫሪስን ይዞ የሂክሶስ ወገን ከግብጽ አውጥቶ ወደ እስያ (ከነዓን) እንደ መለሳቸው ይመስላል። በ19ኛው ሥርወ መንግሥት በአቫሪስ አጠገብ አዲስ ዋና ከተማፒ-ራምሴስ ተሠራ።