የአባሲዶች መንግሥት ግዛትአባሲዶች የሚባሉት የአረቡን ክፍለ ዓለም ከ742-1250 ዓ.ም. የገዙት የነገሥታት ቤተሰቦች ናቸው። እነዚሁምባግዳድ (የአሁኗኢራቅ ዋና ከተማ) ላይ ተቀምጠው ይገዙ የነበሩት የሱኒ እምነት ክፍል አራማጆች ሲሆኑኡማያዶችን ከስልጣን ያስወገዱት ናቸው። ዘራቸው (እንዲሁም መጠሪያቸው) የነብዩ መሃመድ አጎት ከነበረው ከአባስ ኢብን አብደል ሙጣሊብ እንደወረደ ይተረካል።
በ742 ካሊፍነቱን ከተቆናጠጡ በኋላ የመንግስታቸውን መቀመጫ ከደማስቆ (የአሁኗሶርያ ዋና ከተማ) ወደ ባግዳድ አዙረው ለ2 መቶ አመታት ያህል የአረቡን ክፍለ አለም ለመግዛት በቅተዋል። ይሁንና ኋላ ላይ የኦቶማን ቱርኮች መንግሥት እየጠነከረ በመምጣቱ ግዛቶቻቸውን ሁሉ እያጡ ሄደዋል። በመጨረሻም በ1250ሁላጉ ካሃን የተባለው የሞንጎሎች መሪ ባግዳድን ሲበዘብዝ የመንግስታቸው ፍጻሜ ለመሆን በቅቷል። የነዚሁ የአባሲዶች ዘር የሆኑ አል አባሲ የሚሰኙ ጎሳዎች በኢራቅ ውስጥ ከቲክሪት ከተማ ወደ ሰሜን ምስራቅ ሲል በሚገኙ አካባቢዎች አሁንም ሰፍረው ይገኛሉ።
አንድ ሺ ከአንድ ሌሊቶች በተሰኘው የተረቶች መድብል ውስጥ ታሪኩ የሚነገርለትሃሩን አል ረሺድ (በ757 ተወልዶ ከ778-800 ነግሷል) ዘሩ ከአባሲዶች የሚደመር ነው።