Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

አሪያኒስም

ከውክፔዲያ

አሪያኒስም ወይምየአሪያን ቤተ ክርስቲያን በአንድክርስቲያን ቄስአሪዩስ (250-328 ዓም) ትምህርቶች የተመሠረተ በሥላሴ የማያምንሀረ ጤቃዊ የተባለ እምነትና እንቅስቃሴ ነበር።

አሪዩስ እንዳስተማረኢየሱስ ክርስቶስ ወይም ወልድ ከእግዚአብሔር አብ በታች የተለየና የተፈጠረ አምላክ እንደ ነበር አለ፣ እንጂ ሥላሴን አላስተማረም። እግዚአብሔር ከዓለም በፊት ኢየሱስን ቢፈጥርም፣ ኢየሱስ ግን ያልኖረበት ጊዜ ነበር፤ ከአብ በታች የተለየ ንዑስ አምላክ ነው ብሎ ያስተምር ነበር።

አሪዩስ ካረፈ በኋላ አሪያኒስም ለጊዜው በምሥራቁየሮሜ መንግሥት እየተደገፈ እምነቱ ወደ አንዳንድ ጀርመናዊ ብሔር ተስፋፍቶ ነበር፤ ለጥቂት ዘመናት እስከ 663 ዓም ድረስ ቆየ። የ«አሪያኖች» ስም ከመሥራቹ አሪዩስ የተሰየመ ሲሆን፣ አሁን አንዳንድ ያልተማሩ ሰዎች «አርያኖች» ከሚለውሕንዳዊ-ኢራናዊ ስያሜ ጋራ ተስተዋቸዋል፤ በውኑ ግን «አሪያኖች» ከ«አርያኖች» ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም።

ታሪክ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
ራቬና ጣልያን ከ500-550 ዓም ግድም ከአሪያን ቤተክርስቲያን፤ ከዚህ ናሙና በቀር ብዙ ኪነታቸው አይተርፍም።
  • 250 ዓም - አሪዩስ በስሜን አፍሪካ ሊብያ ተወለደ።
  • 252 ዓም - የአንጾኪያ ጳጳስ የሆነውጳውሎስ ዘሳሞሳታ ኢየሱስ እንደ ተራ ሰው ተወልዶ በኋላ በሕይወቱ ሳለ እንደ አምላክ ወይምመሢህ ተቀባ በማለት አስተማረ።
  • 260 ዓም - ጳውሎስ ስለዚያው ተቃራኒ ትምህርት በሲኖዶስ ተሻረ። አንድ ቄስሉቅያኖስ ዘአንጾኪያ ደግሞ በዚህ ምክንያት ተወገዘ።
  • 277 ዓም - ሉቅያኖስ ከቤተ ክርስቲያን ጋራ ተራርቆ እንዲመለስ ተፈቀደ። አሪዩስ በአንጾኪያ የዚሁ ሉቅያኖስ ተማሪ እንደ ሆነ ይታመናል።
  • 295 ዓም - የሮሜ ቄሣሮችዲዮቅሌጥያንጋሌሪዩስ ክርስትናን እንደገና ከለከሉ፣ ክርስቲያኖች ተሰቃዩ።
  • 297 ዓም - አንድ የግብጽ ኤጲስ ቆጶስሜሌቲዩስ ዘሊኮፖሊስ ክርስትናን በስቅይ ምክንያት የካዱት ሰዎች ፪ኛ ወደ ምዕመናን እንዳይገቡ መከልከል ስለ ፈለገ፣ ለዚህ ከባድ አስተያየት እንደ ረባሽ ተሻረ። ቄሱ አሪዩስ ድግሞ በዚሁ ጉዳይ ተከተለው።
  • 303 ዓም - ቀሣሩ ጋሌሪዩስ ሊሞት ሲል ጸጽቶ ክርስትናን እንዲታገሥ ፈቀደ። አሪዩስ የሜሌቲዩስ ደጋፊ ስለ ነበር በእስክንድርያ ጳጳስ ጴጥሮስ ተወገዘ።
  • 305 ዓም - የጴጥሮስ ተከታይ አቡነአኪላስ አሪዩስን ይቅር ብሎ እንደ ቄስ አስመለሰው። ቄሣሮቹቆስጠንጢኖስሊኪኒዩስየሚላኖ ዓዋጅ አውጥተው ክርስትና እንዲታገሥ ንብረታቸውም እንዲመለስ አዘዙ። አኪላስ ከጥቂት በኋላ ዓርፎ አቡናአሌክሳንደር ተከተሉት።
  • 312 ዓም - አሪዩስ የአሪያኒስም ትምህርት በግልጽ አስተምሮ አቡና አሌክሳንደር የእስክንድርያ ሲኖዶስ ጠርቶ ሥላሴን ስለ መካዱ አሪዩስን ወገዘው።
  • 317 ዓም - የአሪያኒስም ክርክር ስላልጠፋ መላው ቤተ ክርስቲያን በንቅያ ጉባኤ ሥላሴን ደግፈውየንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት አወጡ።
  • 328 ዓም - ቤተ ክርስቲያን አሪዩስን ይቅር ብሎ አሪዩስ ወደ ቁስጥንጥንያ ተጉዞ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሳይገባ በኩራቱ ሠልፍ አደረገ፤ በዚህም ሠልፍ ሆድ ዕቃው ዝም ብሎ ወድቆ ሞተ።
  • 329 ዓም - ቆስጠንጢኖስ ሊሞቱ ሲሉ ተጠመቁ፤ የተከታያቸው በምሥራቁ መንግሥትቆስጠንቲዩስ ዝንባሌ ለአሪያኖች ወገን ነበር።
  • 343 ዓም - ቆስጠንትዩስ በመላው ሮሜ መንግሥት ቄሣር ሆኖ በምዕራብም አሪያኒስምን ይገፋ ጀመር።
  • 347 ዓም - ቆስጠንትዩስ በሮሜ ፓፓሊቤሪዩስ ፈንታ ለትንሽ ጊዜ የአሪያን ፓፓ፪ ፌሊክስ አስገባ።
  • 349 ዓም -የሲርሚዩም ጉባኤ አርያኒስምን ደግፎ አብ ከወልድ በላይ ነው በማለት በየነ። ይህ የአሪያኒስም ጫፍ ነበረ።
  • 353 ዓም - የቆስጠንቲዩስ ተካታይዩሊያኖስ ከሓዲ የድሮ አረመኔነት ወዳጅ ሲሆን ክርስትናን ለመቃወም በወገኖቹ መካከል የነበረውን ክርክር አስነሳሳ።
  • 355 ዓም - ዩሊያኖስ በጦርነት አርፎ ክርስቲያን ወታደርዮቪያኑስ ቄሣር ሆኑ።
  • 356 ዓም - ዮቪያኑስ አረመኔነትን ከልክለው ክርስትናንየመንግሥት ሃይማኖት አደረጉት። ከትንሽ በኋላ ዓረፉ። በምሥራቁ ተከታያቸውቫሌንስ የአሪያኒስም ደጋፊ ነው። በምዕራቡ ወንድሙ፩ ቫሌንቲኒያን የሥላሴ ደጋፊ ናቸው።ቫንዳሎች የተባለው ጀርመናዊ ጎሣ ደግሞ አረመኔነትን ትተው የአሪያኒስም ምዕመናን ሆኑ።
  • 368 ዓም -ጎታውያን እናጌፒዶች የተባሉት ጀርመናውያን የአሪያኒስም ምዕመናን ሆኑ።
  • 370 ዓም - ቫሌንስ በጦርነት ዓርፎ ተከታዩ በምሥራቁ፩ ተዎዶስዮስ የሥላሴ ደጋፊ ናቸው።
  • 372 ዓም -የተሰሎንቄ ዐዋጅ የሥላሴ እምነት ወይም ካቶሊክ-ኦርቶዶክስ-ሐዋርያዊ ቤተክርስቲያን በመላው ሮሜ መንግሥት ይፋዊ አደረገው።
  • 373 ዓም -ዮቁስጥንጥንያ ጉባኤ ጸሎተ ሃይማኖት አድሶ ትምህርተ ሥላሴን በይበልጥ ገለጸ።
  • 403 ዓም - ጀርመናዊውየቡርጎኝ መንግሥት የንቅያ ክርስትናን ተቀበለ።
  • 440 ዓም - ጀርመንዊስዌቢ ነገድ የንቅያ ክርስትናን ተቀበለ።
  • 442 ዓም - የቡርጎኝ መንግሥት የንቅያ ክርስትናን ትቶ ወደ አሪያኒስም ቀየረ።
  • 443 ዓም -የከልቄዶን ጉባኤ - የሮሜ ቤተክርስትያን ከሐዋርያዊ (ተዋሕዶ) ቤተክርስቲያን ተለያየ።
  • 458 ዓም - ስዌቢ የንቅያ ክርስትናን ትተው ወደ አሪያኒስም ቀየሩ።
  • 508 ዓም - የቡርጎኝ መንግሥት እንደገና ከአሪያኒስም ወደ ካቶሊክ-ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተመለሰ።
  • 526 ዓም - የአሪያን ቫንዳሎች መንግሥት ለቢዛንታይን መንግሥት ወደቀ።
  • 542 ዓም - ስዌቢ እንደገና ከአሪያኒስም ወደ ካቶሊክ-ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተመለሱ።
  • 545 ዓም - የአሪያንኦስትሮጎታውያን (ምሥራቅ ጎታውያን) መንግሥት ለቢዛንታይን መንግሥት ወደቀ።
  • 559 ዓም - የአሪያን ጌፒዶች መንግሥት ለአቫሮች ወደቀ።
  • 560 ዓም - ከኦስትሮጎታውያንና ከጌፒዶች ቅሬታዎች ጋር ተባብረውሎምባርዶች የተባሉት ጀርመናውያን ጎሣ የአሪያን ክርስትና ምዕመናን ሆኑ።
  • 581 ዓም -ቪዚጎቶች (ምዕራብ ጎታውያን) አሪያኒስም ትተው ካቶሊክ-ኦርቶዶክስ ሆኑ።
  • 595 ዓም - ሎምባርዶች አሪያኒስም ትተው ካቶሊክ-ኦርቶዶክስ ሆኑ።
  • 619 ዓም - ሎምባርዶች እንደገና ወደ አሪያኒስም ተመለሱ።
  • 645 ዓም - ሎምባርዶች ዳግመኛ አሪያኒስም ትተው ወደ ካቶሊክ-ኦርቶዶክስ ተመለሱ።
  • 653 ዓም - ሎምባርዶች ለ፫ኛው ጊዜ በአሪያን ነገሥታት ተገዙ።
  • 663 ዓም - የሎምባርዶች እንዲሁም የአውሮፓ መጨረሻ አሪያን ንጉሥጋሪባልድ አርፎ የአሪያኒስም እምነት ደግሞ ጠፋ።
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=አሪያኒስም&oldid=385448» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2026 Movatter.jp