Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ኒው ዚላንድ

ከውክፔዲያ

ኒው ዚላንድ
New Zealand
Aotearoa

የኒው ዚላንድ ሰንደቅ ዓላማየኒው ዚላንድ አርማ
ሰንደቅ ዓላማአርማ
የኒው ዚላንድመገኛ
የኒው ዚላንድመገኛ
ኒው ዚላንድ በአረንጓዴ ቀለም
ዋና ከተማዌሊንግተን
ብሔራዊ ቋንቋዎችእንግሊዝኛማዎሪ፣ የምልክት ቋንቋ
መንግሥት
{{{

ንግሥት

ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ
ጆን ኪይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
268,021 (74ኛ)

2.1
የሕዝብ ብዛት
የ2010 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2006 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
4,367,700 (123ኛ)

4,027,947
ገንዘብየኒው ዚላንድ ዶላር
ሰዓት ክልልUTC +12
የስልክ መግቢያ+64
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን.nz

ኒው ዚላንድ በደቡብ ምዕራብፓሲፊክ ውቅያኖስ የምትገኝ የደሴት ሀገር ናት።

ቋንቋዎች

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

በኒው ዚላንድ በዋንነት የሚነገረው መደበኛ ቋንቋእንግሊዝኛ ነው።ማዖሪኛ በተለይ በማዖሪ ብሔር ይነገራል፣ በ1979 ዓ.ም. ደግሞ ይፋዊ ቋንቋ ሆነ። ከ1998 ዓ.ም. ጀምሮ የአገሩ ሦስተኛው ይፋዊ ቋንቋየኒው ዚላንድ እጅ ምልክት ቋንቋ ሆኗል።

ባህል

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

ከኒው ዚላንድ ሕዝቦች መካከል የማዖሪ ብሔር ከሁሉ ይልቅ ለረጅም ዘመን በደሴቶቹ ላይ ኑረዋል። ማዖሪዎች «ሃካ» ስለ ተባለው ባህላዊ የውግያ ጭፈራ ታውቀዋል። በኒው ዚላንድ ባሕል ደግሞ የአገሩስፖርት (በተለይ የራግቢ) ቡድኖች ጨዋታ ሳይጀምሩ ሁልጊዜ «ሃካ» ይጨፍራሉ።

አንዳንዴ በቀልድ የኒው ዚላንድ ባህል ዓምዶች «ሦስቱ Rዎች» ይባላሉ - እነሱም «Rugby Racing እና beeR» (ራግቢ፥ እሽቅድድምናቢራ) ናቸው። እንዲያውምየፈረስ እሽቅድድም አሁን እንደ ቀድሞ ደረጃ የተወደደ አልቆየም፣ ራግቢ እና ቢራ ግን ዛሬውንም በኒው ዚላንድ ሕዝብ በኩል በጣም የሚወደዱ ሆነው ቀርተዋል።

የኒው ዚላንድ ሰዎች አንዳንዴ በመጫወት ሲሆን በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ዘንድ «ኪዊዎች» ይባላሉ። «ኪዊዎች» በተለመደው (በጅምላ አመለካከት) ተጨባጭ ያልሆነ ኀልዮ ወይም አሣብ ሳይሆን ተግባራዊ ጉብዝና እና ሙያ ይመርጣሉ። ኒው ዚላንድ ለረጅም ዘመን በክፍሎች ያልተመደበ ሕብረተሰብ ይቆጠር ነበር - ከሃብታሞችና ደሃዎች ኒው ዚላንድ ኗሪዎች መካከል የነበረው ልዩነት ያንስ ነበር ማለት ነው። በቅርቡ ባለፉት አሥርታት ግን ይሄው ሁናቴ ተቀይሯል።

ብዙ የዚው ዚላንድ ኗሪዎች አድገው ወደ ውጭ አገሮች ይጎበኛሉ፣ ብዙዎቹም የባህላዊ ልውውጥ ፕሮግራሞች ይጠቅማሉ፣ ስለዚህ በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ፣ በተለይም በአውስትራሊያብሪታንያአውሮፓእስያ ይጓዛሉ።

ኦሺያኒያ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
አገሮች
በጥገኝነት
(ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍመሠረትወይምመዋቅርነው። እርስዎሊያስፋፉት ይችላሉ!)
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ኒው_ዚላንድ&oldid=343419» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp