Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ታሪክ

ከውክፔዲያ

ታሪክ በትክክል እንደሚሰፈን ከተጻፉት መዝገቦች አንስቶ ይጀምራል። ከዚያ አስቀድሞ ምንም የተጻፉት መዝገቦች ሳይኖሩ የነበረው ወቅትቅድመ-ታሪክ ይባላል።

በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌየመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እናየጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም «ቅድመ-ታሪክ» ነው።

በሌላ አገር ግን የጽሑፍ መዝገቦች እንዲሁም የታሪክ መጋረጃ መከፈቱ እንደ ግብጽ ጥንታዊ አይሆንም። ለምሳሌ ከሜክሲኮ ስሜን የኖሩት ስሜን አሜሪካ ኗሪዎች እንደ ብዙ አሕጉር ሰዎች ለረጅም ዘመን የጽሑፍ አካል ባጠቃላይ ያልነበራቸው ሆነው ቀሩ። ከዚሁ የመዝገቦች ጉድለት የተነሣ ከ1500 ዓም በፊት ያለው ጊዜ ሁሉ የስሜን አሜሪካ ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። ከ1500 ዓም በፊት የተቀረጹት አንዳንድ ጽሑፎች በተለይም የፊንቄ ቋንቋ በሰፊ በአሜሪካዎች ቢገኙም ሁላቸው በፈረንጅ ሊቃውንት አጠያያቂ ተብለዋል። ሆኖም ስለነዚህ የፊንቄ ቅርሶች ወዘተ. በአሜሪካ ተገኝተው የሚገልጹ መጻሕፍት ሊገኙ ይቻላል።

ከግብጽጥንታዊ መንግሥት ዘመን ቀጥሎ ጥንታዊ የሆኑት የኩኔይፎርም ጽሑፍ መዝገቦች ከመስጴጦምያ ከ2500 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ሊታዩ ይቻላል። የአንዳንድ ሌላ አገር መዝገቦች ለምሳሌ የቻይና መዝገቦች በልማድ ተጠብቀው ደግሞ ከዚህ ዘመን ያህል ጀምሮ ይዘግባሉ፤ ነገር ግን በቻይና በሥነ ቅርስ ረገድ ከ1200 ዓክልበ. በፊት የተቀረጸው ጽሑፍ ቢኖር አልተረፈም ወይም አልተገኘም። ከ1600 ዓክልበ. በፊት የነበረውንምየሥያ ሥርወ መንግስት የምናውቀው በኋላ በተዘገቡት ጽሑፎች ብቻ ሲሆን የዚያ ዘመን ታሪክ «አፈ ታሪክ» ሊባል ይችላል።

ደግሞ ይዩ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
(ይህ ታሪክ ነክ ጽሑፍመሠረትወይምመዋቅርነው። እርስዎሊያስፋፉት ይችላሉ!)
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ታሪክ&oldid=359914» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp