Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ቤኒን

ከውክፔዲያ

République du Bénin
የቤኒን ሪፐብሊክ

የቤኒን ሰንደቅ ዓላማየቤኒን አርማ
ሰንደቅ ዓላማአርማ
ብሔራዊ መዝሙር: L'Aube Nouvelle

የቤኒንመገኛ
የቤኒንመገኛ
ቤኒን በቀይ ቀለም
ዋና ከተማፖርቶ ኖቮኮቶኑ
ብሔራዊ ቋንቋዎችፈረንሳይኛ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
 
ፓትሪስ ታሎን
ዋና ቀናት
ሐምሌ ፳፭ ቀን፲፱፻፶፪ ዓ.ም.
(August 1, 1960 እ.ኤ.አ.)
 
ነጻነት ከፈረንሳይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
114,763[1] (100ኛ)

0.4
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2013 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
10,653,654[2] (84ኛ)

10,008,749
ገንዘብምዕራብ አፍሪካዊ CFA ፍራንክ
ሰዓት ክልልUTC +1
የስልክ መግቢያ+229
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን.bj

ቤኒን ወይም በይፋየቤኒን ሪፐብሊክምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከምዕራብቶጎን፣ ከምሥራቅናይጄሪያን እና ከሰሜንቡርኪና ፋሶኒጄርን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋፖርቶ ኖቮ ሲሆን የመንግሥቷ መቀመጫ ግንኮቶኑ ከተማ ናት። የቤኒን የቆዳ ስፋት ወደ 110,000 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሆን የሕዝቧ ብዛት ደግሞ ወደ 9.05 ሚሊዮን ይገመታል።

የቤኒን ይፋ ቋንቋፈረንሳይኛ ሲሆን እንደፎንዮሩባ የመሳሰሉት የሀገሪቷ ባህላዊ ቋንቋዎች ሰፊ ተናጋሪ አላቸው።የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ብዙ ተከታዮች ሲኖሩት እስላሞች፣ ፕሮቴስታኖችና የቩዱ ተከታዮችም ይገኛሉ። ቤኒንየተባበሩት መንግሥታትየአፍሪካ ሕብረት እናም ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ናት።

ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. የሀገሪቱ መሬት በዳሆሚ መንግሥት ነበር የሚመራው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአካባቢው ሰፍቶ ስለነበር ቦታው የባሪያ ጠረፍ ይባል ነበር። በ1892 እ.ኤ.አ. ፈረንሳይ አካባቢውን በመቆጣጠርየፈረንሳይ ዳሆሚ ብላ ሰየመችው። በ1960 እ.ኤ.አ. ዳሆሚ ነፃነቷን በማግኘት ለ፲፪ ዓመታት በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ተመርታለች።

ከ1972 እስከ 1990 እ.ኤ.አ. ሀገሪቷ በማርክሲስት ሌኒኒስት አቋምየቤኒን ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ተብላ ተሰመች። በዚህ ጊዜ በሀገሪቷ የኢኮኖሚ ውድቀት ተከስቶ ነበር። በ1991 እ.ኤ.አ. የቤኒን ሪፐብሊክ ተመሠረተ።

ቤኒን ወደ ውጭ የሚልከው ዋንኛ ምርትጥጥ ሲሆን ከዚህ በላይካሸው ለውዝ (Anacardium occidentale)፣ኮኮነትዓሳእንጨት ወደ ውጭ ይላካሉ።ፔትሮሊየምወርቅም ይላካሉ። ባለፉት ዓመታት ውስጥ ቤኒን ለተግባራዊሳይንስ ምርመራ ጥናት አንጋፋ ማዕከል ሆናለች።

በደቡብ ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ የበቆሎዳቦኦቾሎኒ ወጥ ወይም በቲማቲም ወጥ ይጠቀማል።አሳ እናዶሮ ከሁሉ ተራ ሥጋዎች ናቸው፣በሬፍየልየጫካ አይጥ ደግሞ ይበላሉ። በስሜን ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይኮቴሃሬ በበቆሎው ፈንታ ይጠቀማል። ቤሬ ወይምአሳማ በጥብስ ወይም በወጣወጥ፣ፎርማጆኩስኩስሩዝባቄላፍራፍሬ በሰፊው ይጠቀማሉ።

እግር ኳስ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥቤስቦል ወደ ቤኒን ገብቷል።

ማጣቀሻ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]
  1. (PDF)Demographic Yearbook – Table 3: Population by sex, rate of population increase, surface area and density.United Nations Statistics Division.2012.http://unstats.un.org/unsd/demographic/products/dyb/dyb2012/Table03.pdf በ3 September 2017 የተቃኘ. http://unstats.un.org/unsd/demographic/products/dyb/dyb2012.htm
  2. http://www.insae-bj.org/Migration.html?file=files/stats-demographiques/STATISTIQUES%20DEMOGRAPHIQUES.xlsx
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለቤኒን የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።


አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
Map indicating Western Africaምዕራብ አፍሪቃ
Map indicating Northern Africaስሜን አፍሪቃ
Map indicating Central Africaመካከለኛ አፍሪቃ
Map indicating Eastern Africaምሥራቅ አፍሪቃ
Map indicating Southern Africaደቡባዊ አፍሪቃ
 በጥገኝነት፡
 ዕውቅና ያልተሰጠ፡
1 ኹኔታው ያልተረጋገጠ ነው። 2 ግዛቱ በከፊል በእስያ ነው። 
(ይህ አጭር መልክዐ ምድር ነክ ጽሑፍመሠረትወይምመዋቅርነው። እርስዎሊያስፋፉት ይችላሉ!)
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ቤኒን&oldid=345044» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2026 Movatter.jp