የቤሲክ አረፍተ የመስመር መቀጠያ ፊደል ከሌለ መስመር መጨረሻ ላይ ያልቃሉ። በጣም አነስተኛ ቤሲክ LET, PRINT, IF andGOTO የሚሉት ትእዛዞች ይበቁታል::
የመስመር ቁጥሮች የቤት ኮምፒውተር ቤሲክን ከሚለዩ ገጽታዎች አንዱ ነው። አንዳንድ ቆይተው የመጡ የቤሲክ ተርጓሚዎች (interpreters) አምበሮ የሚመጡ RENUMBER የሚባል መስመር ቆጣሪ ትእዛዝ ነበራችው ።
አንዳንድ ዘምዝናዊ ባሲኮች የመስመር ቁጥርን ትተው አብዛኛው በሌሎች ቋንቋዎች (እንደሲ ናፓስካል) የሚታወቁትን የመዝገብና (data) የመቆጣጠሪያ (control) አቀማመጥን አስገብተዋል። (አንዳንድ በመስመር ቁጥር ላይ የተመሰረቱም ቋንቋዎች እነዚህን አቀማመጦች ማስገባታችውን መመዝገብ ያሻል።)
- do - loop - while - until - exit
- onx goto / gosub (switch & case)
በቅርብ የተሰሩ እንደቪሱአል ቤሲክ (Visual Basic) የቤሲክ ተዛማጆችእቃ አዘል ገጽታዎችን እንደ For Each...Loop ያሉ አቀማመጦችን ሰብስቦችና ተርታዎችን በጥምዝ (loop) ለመፈተሽ ቪሱአል ቤሲክ 4 አንስቶ ሲያስገቡ ብእቃ አዘለ ፍርግምናውርስ ተብሎ የሚታወቀውን አሰራር በመቅረብ አስገብተዋል። የማህደረ እውስታ (memory) አስተዳደር ዘዴው ካብዛኛው የተደራጁ ቋንቋዎች የቀለለ ነው። ይህም ሊሆን የቻለው ቋንቋውgarbage collection ወይምየቆሻሻ ሰብሳቢ ይዞ ስለሚመጣ ነው::
ቤሲክ እንደ ሲ የውጭ ቤተ መጻህፍት (external library) የለውም። የቋንቋው ተርጓሚ (interpreter) ሰፊ ቤተ መጻህፍትና አብረውት የተገነቡ ፕሮሲጀሮች (procedures) ይይዛል: ለነዚህ ፕሮሲጀሮች አንድ ፈርጋሚ ሙያውን ለመማርም ሆነ ቀለል ያሉ ፕሮግራሞችን ለመጻፍ የሚያስፈልጉትን አብዛኞቹን መሳሪያዎች (የሂሳብ ተግባሯትን፥ የፊደል ክር-string, የማስገቢያና የማሶጪያ መስኮት፥ የስዕልና የመዘገብ መሳሪያ) ያካትታል።አንዳንድ የቤሲክ ቤተሰብ አባል ቋንቋዎች ፈርጋሚው የራሱን ፕሮሲጀሮች እንዲጽፍ አይፈቅዱም:: ፈርጋሚው ከአንድ ቅርንጫፍ ወደሌላ ለመዘዋወር በዛት GOTOን በመጠቀም ፕሮግራሙን ይጽፋል። የዚህ ውጤት ደግሞ ለአንባቢ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ የፕሮግራም ምንጭ (source)፥ በተለምዶ "እንደ ፓስታ የተወሳሰበ" ወይምspagetti code፥ አይነት ይሆናል። GOSUB የቅርንጫፍ ዝውውሩን የሚያደርገው ወደ ንዑስ ክንውኖች (አነስተኛ የፕሮግራም አካሎች) ሲሆን ባብዛኛው ያለግቤት (parameters)ና ያለሰፈር ተለዋጭ (local variable) ነው። ዘመናዊ የቤሲክ ስሪቶች እንደ ሚክሮሶፍት ኪክ ቤሲክ ሙሉ ንዑስ ክንውኖችንና (subroutines) ተግባራትን (functions) አስገብተዋል። ይህ ቤሲክ ከሌሎች ቋንቋዎች የሚለይበት አንዱ ገጽታው ነው። ቤሲክ፥ እንደ ፓስካል፥ መልስ በማይጠበቅባቸው ፕሮሴጀሮችና (ንዑስ ክንውኖች የምንላቸው) መልስ በሚሰጡት (ተግባራት) መሃከል ልዩነት ያደርጋል። ሌሎች እንደ ሁሉንም በተግባራት ስያሜ (አንዳንዶቹን ባለ ባዶ መልስ በማለት) ለዩነትን አያደርጉም።
ቤሲክ ለፊደል ክሮች (strings) ስሪ የሚያገለግሉ ጥሩ ተግባራት ያለው ቋንቋ እንደሆነ ይታወቃል። የቀድሞው የዚሁ ቤተሰብ ቋንቋዎች እንደ (LEFT$, MID$, RIGHT$) የመሳሰሉት መሰረታዊ ተግባራት በማቀፍ የፊደል ክሮችን የሚመለከቱትን ስራዎች ያቃልላሉ። የፊደል ክሮች የለት ተለት ስራዎች ላይ በተደጋጋሚ ሰላሚያጋጥሙ ከሌሎች የዘመኑ ቋንቋዎች በዚህ ረገድ ብልጫ አሳይቷል።
የቀድሞው የዳርትሙንት ቤሲክ ለቁጥርና ለፊደል ክር አይነቶችን ብቻ ድጋፍ ይሰጥ ነበር። የሙሉ ቁጥሮች (integers) አይነቶች አልነበሩም። ቁጥሮች በሙሉ ባለነጥብ (floating points) ነበሩ። የፊደል ክሮች አለ ተለዋዋጭ ርዝመት ነበሩ። ቤሲክ የፊደል ክርም ሆነ የቁጥር ተርታዎችን (arrays) እንዲሁ ባለሁለት ማአዘን ተርታዎችን የሚደግፍ ወይም የሚይዝ ቋንቋ ነበር።
ማንኛው ዘምዝናዊ የቤሲክ ቤተሰብ ቋንቋ ቢያንስ ቁጥሮችንና የፊደል ክሮችን ይይዛል። ...
ጀማሪ የቤሲክ ፈርጋሚዎች የቤት ኮምፒውትሯቸው ላይ የሚጀምሩት በከርኒጋንና ሪቺ አማካኝነት እውቅና ያገኘውንሰላም አለም ፍርግም አይደለም። ይልቁኑ የሚቀጥለውን የማያባራ ጥምዝ የሚመስል ነው።
10 PRINT "BOB IS AWESOME!"20 GOTO 10
ክላሲክ ወይም የቀድሞው ቤሲክ፤ ይህ ምሳሌ በስራአት የተደራጀ መሆኑን GOTO ን መጠቀም የግድ ወደተመሰቃቀለ የፍርግም እንደማያመሯ ያሳያል።
10 INPUT "What is your name: "; U$ 20 PRINT "Hello "; U$ 30 REM 40 INPUT "How many stars do you want: "; N 50 S$ = "" 60 FOR I = 1 TO N 70 S$ = S$ + "*" 80 NEXT I 90 PRINT S$ 100 REM 110 INPUT "Do you want more stars? "; A$ 120 IF LEN(A$) = 0 THEN GOTO 110 130 A$ = LEFT$(A$, 1) 140 IF (A$ = "Y") OR (A$ = "y") THEN GOTO 40 150 PRINT "Goodbye "; 160 FOR I = 1 TO 200 170 PRINT U$; " "; 180 NEXT I 190 PRINT
"ዘምዝናዊ" የተደፘጀው ቤሲክ (ለምሳሌ፥ኩኢክቤሲክ ናፓወርቤሲክ), GOTO የተሰኘውን ቃል በዘመናዊ ቃላት ተክተው።
INPUT "What is your name"; UserName$PRINT "Hello "; UserName$DO INPUT "How many stars do you want"; NumStars Stars$ = "" Stars$ = REPEAT$("*", NumStars) ' <- ANSI BASIC--or-- Stars$ = STRING$(NumStars, "*") ' <- MS BASIC PRINT Stars$ DO INPUT "Do you want more stars"; Answer$ LOOP UNTIL Answer$ <> "" Answer$ = LEFT$(Answer$, 1)LOOP WHILE UCASE$(Answer$) = "Y"PRINT "Goodbye ";FOR I = 1 TO 200 PRINT UserName$; " ";NEXT IPRINT