Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ሴሮሕ

ከውክፔዲያ
ሴሮሕ በ1545 ዓ.ም. ለሳለው ለጊዮም ሩዊ እንደ መሰለው

ሴሮሕ (ዕብራይስጥ፦ שְׂרוּג /ሢሩግ/) በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት የራግው ልጅና የናኮር አባት ነበረ።

ዘፍጥረት 11፡22-23 ስለ ሴሮሕ እንደሚለው፣ የሴሮሕ ዕድሜ 130 ዓመት ሲሆን ናኮርን ወለደ፣ ከዚያም ሴሮሕ 200 ዓመት ኖረ። እነዚህ ቁጥሮች ከግሪኩ ትርጉም ሲገኙ የዕብራይስጥናሳምራዊው ትርጉም ቁጥሮች ግን ይለያያሉ። በእብራይስጥ ትርጉም በ30 ዓመት ናኮርን ወለደ፣ ከዚያም 200 ዓመት ኖረ፤ በሳምራዊውም በ130 ዓመት ናኮርን ወለደ፣ ከዚያም 100 ዓመት ኖረ።

መጽሐፈ ኩፋሌ 10፡22-26 ዘንድ፣ ሴሮሕ ከአባቱ ራግውና ከእናቱ ዑራ በ1687 አመተ አለም ተወለደ። በዚያውም አመት ጦርነትና ባርነት በምድር ላይ እንደገና ጀመረ፤ ደግሞ የሴሮሕ አያት ዑር ያንጊዜየከላውዴዎን ዑር የተባለውን አምባ ሠራ። ጣኦታትም ይሠሩ ጀመር። የኖኅ ልጆችም ባሕል በፍጹም ስለ ተዛባ የሴሮሕ ስም «ሴሮክ» ሆነ ይላል። በ1744 አ.አ. ሴሮሕ ሚስቱን ሚልካ አገባ፤ እርሷም የካቤር ልጅና የፋሌቅ ልጅ-ልጅ ትባላለች። በዚያም አመት ሚልካ ልጁን ናኮርን ወለደችለት፤ ስለዚህ እድሜው 57 ዓመታት ነበረ። ሴሮሕም ልጁም ናኮርን በዑር ከተማ አሳደገው፤ የጨረቃ ሟርት አስተማረውም።

ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ሴሮሕ&oldid=307881» የተወሰደ
መደብ:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp