ማዖሪ ቋንቋ (Māori ወይምTe Reo Māori /ቴ ሬዖ ማዖሪ/፣ በአጭሩTe Reo «ቋንቋው») ከኒው ዚላንድ መደበኛ ቋንቋዎች አንዱ ነው። የምሥራቅፖሊኔዚያ ደሴቶች ቋንቋ ቤተሠብ አባል ሲሆን የታሂቲ እና የሃዋይኢ እንዲሁም የሳሞዓ እና የቶንጋ ቋንቋዎች ዘመድ ነው። የተናጋሪዎቹ ቁጥር 100,000 የሚያሕል ነው።
ኒው ዚላንድ አሁን ሦስት መደበኛ ቋንቋዎች ያሉት ማዖሪ፣እንግሊዝኛና የኒው ዚላንድ እጅ ቋንቋ ናቸው። ስለዚህ አብዛኛው የመንግሥት ዘርፎች ሁለት ስሞች አላቸው፤ ለምሳሌ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርDepartment of Internal Affairs (/ዴፓርትሜንት ኦቭ ኢንተርናል አፈይርዝ/) በእንግሊዝኛ፣ ደግሞምTe Tari Taiwhenua (/ቴ ታሪ ታይፌኑዋ/) በማዖሪ ተብሎ ይታወቃል። ከመጋቢት1996 ዓ.ም. ጀምሮ የማዖሪቴሌቪዥን አገልግሎት በመንግስት እርዳታ ኖሯል።
ማዖሪ ወደ ኒውዚላንድ ያመጡት ፖሊኔዝያውያን ሰዎች ከሌሎች ደሴቶች የደረሱ ምናልባት በታንኳ ነበር። ከ1860ዎቹ በኋላ ግን እንግሊዞች በኒው ዚላንድ በሠፈሩበት ጊዜ እንግሊዝኛ አመጡና ትምርት ቤቶች ሲከፈቱ ከ1880ዎቹ የማዖሪ ጥቅም በትምህርት ቤት ውስጥ ተከለከለ። በዚህ ብዙዎች የማዖሪ ሕዝብ እንግሊዝኛ በግዴታ ተማሩ። ነገር ግን እቤት ውስጥ፥ በአምልኮት፥ በፖለቲካ ስብሰባ ወዘተ. የማዖሪ ቋንቋ መናገሩ ፈጽሞ አልተቋረጠም። ከዚያ በላይ አንዳንድ የማዖሪ ጋዜጣም ሆነ መጽሐፍ ይታተም ነበር። በ1980ዎቹ 20 ከመቶ ማዖሪዎች ብቻ እንደ ኗሪ ቋንቋ ይችሉት ነበር። በዚያን ጊዜ ቋንቋው ለዘለቄታ እንዳይጠፋ አዲስ የማዖሪ ቋንቋ እንቅስቃሴ ተጀመረና የማዖሪ ትምህርት ቤቶች ተከፈቱ።
ማዖሪ የሚጻፍበት በላቲን ጽሕፈት አይነትአልፋቤት ሲሆን ፊደሎች እንዲህ 20 ናቸው፦
A Ā E Ē H I Ī K M N O Ō P R T U Ū W NG እና WH
ሁላቸው እንደ ተለመደ ድምጾች አላቸው 'WH' የሚያሰማው ድምጽ ግን እንደ 'ፍ' ይመስላል።
የአብዛኛው ስሞች ቁጥር የሚታይበት ዘዴ የተወሰነ መስተጻምር በመለወጡ ነው። ለነጠላ ቁጥር መስተጻምሩ te 'ቴ' ሲሆን ለብዙ ቁጥር nga 'ንጋ' ይሆናል። ስለዚህ፦
- ika (ኢካ) - ዓሣ፤rākau (ራካው) - ዛፍ
- te ika (ቴ ኢካ) - ዓሣው፤te rākau (ቴ ራካው) - ዛፉ
- ngā ika (ንጋ ኢካ) - ዓሦቹ፤ngā rākau (ንጋ ራካው) - ዛፎቹ
- Kia ora ኪያ ዖራ - ሰላምታ፤ እግዜር ይስጥልኝ
- Hei konei ኸይ ኮነይ - ደህና ዋል / ዋይ
- Kei te pēhea koe ከይ ቴ ፔኸያ ኮዌ - እንደምን ነህ / ነሽ?
- Kei te (tino) pai ahau ከይ ቴ (ቲኖ) ፓይ አሃው - እኔ (በጣም) ደህና ነኝ
Wikipedia- Biggs, Bruce (1994).Does Maori have a closest relative? In Sutton (Ed.)(1994), pp. 96–-105.
- Biggs, Bruce (1998).Let's Learn Maori. Auckland: Auckland University Press.
- Clark, Ross (1994).Moriori and Maori: The Linguistic Evidence. In Sutton (Ed.)(1994), pp. 123–-135.
- Harlow, Ray (1994).Maori Dialectology and the Settlement of New Zealand. In Sutton (Ed.)(1994), pp. 106–-122.
- Sutton, Douglas G. (Ed.) (1994),The Origins of the First New Zealanders. Auckland: Auckland University Press.