Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ልውውጠ ሰብል

ከውክፔዲያ

ልውውጠ ሰብልግብርና ማለት ልዩ ልዩ ምርቶች በተከታታይ ወራቶች በልዩ ልዩ እርሻዎች የማዛወር ዘዴ ነው። አንድ ሰብል በአንዱ እርሻ በየዓመቱ ከመተክል ይልቅ የልውውጠ ሰብል ዘዴ ለመሬቱ (ላይ አፈር) እንዳይደክምበት እጅግ ይሻላል።

አውሮፓ ከ800 ዓ.ም. በፊት የሁለት እርሻ ልውውጠ ሰብል በሰፊ ይጠቀም ነበር። በዚህ ዘዴ ግማሹ መሬት በአንድ አመት ሲተክል ሌላው ግማሽ አርፎ አደር ይቀራል። በሚከተለውም አመት ይገለበጡ ነበር።

ከ800 ዓ.ም. በኋላ የሦስት እርሻ ልውውጠ ሰብል ይስፋፋ ጀመር። አንዱ እርሻ በስንዴ፣ ሁለተኛውም በአተርምስር ወይምባቄላ፣ ሦስተኛውም አርፎ አደር ቀረ። በሚከተለው አመት የእርሻ ሚናዎች ተለዋወጡ። አተር ምስርና ባቄላ በተለይ ለአፈሩም ሆነ ለሰዎች የተሻለ ምግብ ይሰጣሉ። ስንዴ የአፈርናይትሮጅን ሲፈጅ፣ ባቄላ ግን ናይትሮጅን ይመልሰዋል።

ከ1500 እስከ 1900 ዓ.ም. ድረስ በአውሮፓ ገበሬዎች የ3 እርሻ ልውውጠ ሰብል ሲጠቀሙ በአንዱ እርሻ ስንዴ፣ በአንዱምገብስ ወይምኣጃ፣ ሦስተኛውም አርፎ አደር ይለዋወጡ ነበር። በዚህ ዘመን ደግሞ የአራት እርሻ ልውውጠ ሰብል ይስፋፋ ጀመር። በዚህ ዘዴ አራቱ ሰብሎች ይለዋወጣሉ፣ እነርሱም ስንዴዱባ ገብስና ሣር (ለመኖ) የሚመስል ናቸው። ይህ ለግብርና ዘዴ ለምርት ትልቅ ማሻሻል ሆነ።

ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ልውውጠ_ሰብል&oldid=310439» የተወሰደ
መደብ:

[8]ページ先頭

©2009-2026 Movatter.jp