Movatterモバイル変換


[0]ホーム

URL:


Jump to content
ውክፔዲያ
ፍለጋ

ሄሮዶቶስ

ከውክፔዲያ
የሄሮዶቶስ ሃውልት

ሄሮዶቶስ ወይምሄሮዶቱስ (ግሪክΗρόδοτος) የጥንታዊ ግሪክ (492-433 ዓክልበ.)ታሪክ ጸሓፊ ነበረ። የታሪክ መረጃዎቹን በሥርዓት በመሰብሰብ እና በማቀናበሩ የታሪክ-አባት በመባል ይታወቃል።

ኢትዮጵያ በሄሮዶቶስ

[ለማስተካከል |ኮድ አርም]

«ሂስቶሪያይ» (ታሪኮች) በሚባል ጽሑፍ (472 ዓክልበ. ገደማ) ሄሮዶቶስ ስለ «ኢትዮጵያ» ጥንታዊ መረጃ አቅርቧል። በሄሮዶቱስ አስተያየት ኢትዮጵያ ከኤለፋንቲን ደሴት (የአሁኑአስዋን) ጀምሮ ከግብጽ ወደ ደቡብ የሚገኘው አገር ሁሉ ነው። በወርቅየዝሆን ጥርስዞጲ እንጨት ሀብታም አገር ነው። አንድ ዋና ከተማ በሜሮዌ አላቸው፤ እዚያ አማልክታቸውዜውስ እናዲዮናስዮስ ብቻ ናቸው ይላል። በፈርዖን1 ፕሳምቲክ ዘመን (650 ዓክልበ. ገደማ) ብዙ የግብጽ ወታደሮች አገራቸውን ከደው በኢትዮጵያውያን መካከል እንደ ሰፈሩ ይላል። ከግብጽ 330 ፈርዖኖች፣ 18ቱ ኢትዮጵያውያን (ማለት የኩሽ ፈርዖኖች) ነበሩ ብሎ ጻፈ።ግዝረት ከሚፈጽሙት አገሮች አንድ መሆናቸውን ይመስክራል።

የፋርስ ንጉሥካምቢስስ (570 ዓክልበ. ገደማ) ሰላዮችን ወደ ኢትዮጵያውያን እንደ ላከ ሄሮዶቶስ ይነግረናል። ጠንካራና ጤነኛ ሕዝብ አገኙ። ካምቢስስ ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ ቢዘምትም በቂ ስንቅ ባለማዘጋጀታቸው ለሥራዊቱ በፍጹም አልተከናወነምና ቶሎ ተመልሱ።


ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍመሠረት ወይምመዋቅር ነው።አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ!
ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ሄሮዶቶስ&oldid=378408» የተወሰደ
መደቦች:

[8]ページ先頭

©2009-2025 Movatter.jp